
ጥቅስ
ጌታዬ
እግዚአብሔር ሆይ
እስከዚህ ያደረስኸኝ
እኔ ማን ነኝ ?
ቤቴስ ምንድር ነው?
2 ሳሙ 7፥18
እግዚአብሔር ሆይ
እስከዚህ ያደረስኸኝ
እኔ ማን ነኝ ?
ቤቴስ ምንድር ነው?
2 ሳሙ 7፥18
Sunday, 28 October 2012
አቡነ እየሱስ ሞአ
አቡነ እየሱስ
ሞአ
ገድለኛው አባ እየሱስ ሞአ ህዳር 26 አረፉ። የተወለዱት ጎንደር ጎርጎራ ልዩ ስሙ ዳህና ሚካኤል በ 1196
ዓ/ም ነው፤ በ 30 ዓመታቸው መንነው ደብረ ዳሞ ሄዱ ፤ በአባ ዮሐኒ እጅ መነኮሱ በተጋድሎም ኖሩ፤ ከዚያም ቅዱስ ገብርኤል
እየመራቸው ሐይቅ እስጢፋኖስ መጡ፤ ሐይቅ እስጢፋኖስ ማለት ከደሴ 30 ኪሎ ሜትር ርቆ የሚገኝ ሲሆን የመሰረቱት ካልዕ ሰላማ
የተባሉ ግብጻዊ ጻድቅ ናቸው፤ ገዳሙን ከሰሩ በኃላ የማንን ታቦት እናስገባ ብለው ሲያስቡ ቶራ የምትባል እንስሳ ጭነት ተጭና
ከመካከላቸው ተገኘች፤ ጭነቱን አውርደው ቢያዩት በሐር ጨርቅ የተጠቀለለ ሁለት ታቦት አገኙ አንዱ የእስጢፋኖስ አንዱ
የጊዮርጊስ " ይህንን ታቦት በእየሩሳሌም የሚኖሩ የተሰወሩ ቅዱሳን ከእግዚያብሔር ታዘው የላኩት ነው" የሚል ጽሑፍም አገኙ
ይላል።

Sunday, 21 October 2012
Friday, 19 October 2012
†♥†አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ†♥†
†♥†አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ†♥†
†♥†
“በስመ ሥላሴ”†♥†
†♥†
“እግዚአብሔር
ያፈቅሮሙ
ለጻድቃን
እግዚአብሔር
የዐቅቦሙ
ለፈላስያን፡፡“
(እግዚአብሔር
ጻድቃንን
ይወድዳል፤
እግዚአብሔር ስደተኞችን
ይጠብቃል፡፡)“”†♥†
መዝ.፻፵፭፡፰ (145፡8)
†♥†አቡነ
እስትንፋሰ ክርስቶስ†♥†
ነብየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት ጆሮውን ወደ ልመናቸው አዘነበለ እንዳለ መዝ 33፤29 እግዚአብሔር አምላክ በዓይነ ምህረት ተመለከታቸው ልመናቸውንም ሰምቶ አባታችን አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ሚያዚያ 8 ቀን ተጸንሶ ታህሳስ 9 ቀን ተወለደ፡፡ በተወለደ እለትም ተነስቶ በእግሩ ቆሞ 3 ጊዜ ስብሐት ለአብ ስብሐት ለወልድ ስብሐት ለመንፈስ ቅዱስ ብሎ ጣዕም ባለው አንደበቱ ተናገረ፡፡ 9 ጊዜም ህጻናትን ለሚያናግሩ ገዥ ለሚሆኑ ለአጋይዝተ አለም ሥላሴና ለእመቤታችን ለመስቀሉም ሰገደ፡፡ እዚያ ተሰብስበው የነበሩ ብዙ ሰዎች ከህጻኑ አንደበት የስላሴን ምስጋና ሰምተው ፈጽመው አደነቁ ዳግመኛም በዚህ ህጻን ላይ የእግዚአብሔር ጸጋ አድሮበታል ብለው እየተጨዋወቱ ወደ ሀገራቸው ገቡ፡፡
Tuesday, 16 October 2012
ብፁእ አባታችን አቡነ ዘርዐ ቡሩክ
በረከታቸዉ ይደርብንና ብፁእ አባታችን አቡነ ዘርዐ ቡሩክ ከአባታቸዉ ከቅዱስ ደመ ክርስቶስ ከናታቸዉ ከቅድስት ማርያም ሞገሳ በ 8 ኛዉ መቶ ክ/ዘመን መጨረሻ በክብር ተወለዱ ከመወለዳቸዉ አስቀድሞ ቅድመ አያታቸዉ ከኔ ዘር 7ኛ ትዉልድ አንዲት ሴት ትወልዳለች ከርሶም አለምን በጸሎቱ የሚያድን ይወለዳል ብለዉ ትቢት ተናግረዉላቸዉ ነበር፡፡ በተወለዱ በ 7 አመታቸዉ ይህን አለም ክፋቱን እንዳላይ አይኖቸን አሳዉርልኝ
Subscribe to:
Posts (Atom)