ጥቅስ

ጌታዬ
እግዚአብሔር ሆይ
እስከዚህ ያደረስኸኝ
እኔ ማን ነኝ ?
ቤቴስ ምንድር ነው?
2 ሳሙ 7፥18

Monday 6 July 2015

ምሥጢረ ተክሊል (ክፍል ሰባት , ክፍል ስምንት,ክፍል ዘጠኝ

                                                                           ምሥጢረ ተክሊል ክፍል ሰባት

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
የወደደን የፍቅር መምህራችን እግዚአብሔር ስለማይነገር ስጦታው ሁሉ ስሙ የተመሰገነ ይሁን፤ የአምላክ እናት ቤዛዊተ ዓለም ድንግል ማርያም በትውልዱ ሁሉ አንደበት ምስጋና ይድረሳት፤ ለስሙ ለተለዩ ቅዱሳን፤ ለስሙ ለሞት ተላልፈው ለተሰጡ ሰማእታት፤ መናፍቃንን ድል ለነሱ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን፤ ስለ ስሙ ለተሰደዱ ጻድቃን ምስጋና ይሁን፡፡ አሜን፡፡
እርሱ እየረዳን፤እርሱ ድካማችንን እያገዘን፤እርሱ ጎዶሏችንን እየሞላ፤እርሱ ጥያቄዎቻችንን እመለሰ፤እርሱ በጉዟችን ሁሉ ከፊት እየቀደመ ከኋላም እየተከተለ፤ከጎንም እየደገፈን፤ኃይላችን እያደሰ፤በየምዕራፉ እያሳረፈን ከሰባተኛው ክፍል አድርሶናል፡፡ በእውነት ይህም በእርሱ ነውና ክብር ብቻውን አምላክ ለሆነው ለእርሱ ለእግዚአብሔር ይሁን፡፡ አሜን፡፡
ወዳጆቼ እንደ ውቂያኖስ የጠለቀ እንደ ባሕር የሰፋውን የእናት ቤተክርስቲያናችንን ምስጢራት በማንኪያ ታህል እንድንቀምስ የረዳን እግዚአብሔር በክፍል አንድ የምሥጢረ ተክሊል ምንነት፤ በክፍል ሁለት የጋብቻ ዓላማ፤ በክፍል ሦስት ቅድመ ጋብቻን፤በክፍል አራት የቅድመ ጋብቻን የመጨረሻ ክፍል፤በክፍል አምስት ድንግልናና ተክሊል ፤ በክፍል ስድስት የሥርዓተ ተክሊል መስፈርቶች ምንድን ናቸው? በሚሉ ንዑሳን ርዕሶች እርሱ