ጥቅስ

ጌታዬ
እግዚአብሔር ሆይ
እስከዚህ ያደረስኸኝ
እኔ ማን ነኝ ?
ቤቴስ ምንድር ነው?
2 ሳሙ 7፥18

ጽድቃን፥ሰማዕታት


አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ
ቀኑ መጋቢት 5 ዕለቱ ቅዳሜ ለእሁድ አጥቢያ ሰዓቱ ከሌሊቱ ስድስት ሰዓት ሆኗል፤ አሁንም ህማሙን እየታገለ እያላበው በድካም ለፍጥረቱ ሁሉ ይለምናል፤ “አቤቱ ህዝብህን አድን ርስትህን ኢትዮጰያንም ባርክ” ይላል። ህመም የጀመረው መጋቢት 3 ዓርብ ቀን ነው፤መታመሙን የሰሙ እንደርሱ ቅዱሳን የሆኑት ዘርአ ቡሩክ፤ ፍሬ ቅዱስ፤ያዕቆብ፤ብንያምና ዮሴፍ እንዲሁም በወቅቱ የኢትዮጰያ ንጉስ የነበረው እንድርያስ ሊጠይቁት ተሰብስበዋል ወደ አጠገቡ መድረስ ግን አልተቻላቸውም አባታችን ገብረመንፈስ ቅዱስ የሚጋርደው እንጨት ዛፍ በሌለበት በርሃ እንደ አንበሳ ተኝቶ አዩት በላዩ ያረፈው የእግዚያብሔር ጸጋ ከፊቱ የሚወጣው ብርሃን ቀይ መልኩ ረዥም የራስ ጠጉሩ እንደ ነጭ ሐር የሚሆን ጽሕሙ አስደነቃቸው። ከሌሊቱ ሰባት ሰዓት ሲሆን ከሰማይ ታላቅ ነጎድጓድ ድምጽ ተሰማ ጌታችን መላአክትን አስከትሎ ወደ አባታችን ወረደ፤ ከሰማይ ወደ ምድር ህብሩ አምሳያው ልዩ ልዩ የሆነ እንደ ጸሐይና እንደ ጨረቃ የሚያበራ እንደ ወንጪፍ ድንጋይ ይወረወር ነበር ከዚያ የነበሩ ሁሉ ፈሩ ወደ ኃላም ሸሹ ምድር ራደች ተራሮች ኮረብቶች ተናወጡ ብርቱ ጩኸት ንውጽውጽታ ሆነ። “ወዳጄ ገብረመንፈስ ቅዱስ ሰላም ላንተ ይሁን” እነሆ የማይታበል ቃል ኪዳን እገባልኃለው ስምህን የጠራ መታሰቢያህን ያደረገውን፤ እጣን ቋጥሮ ግብር ሰፍሮ መባ ይዞ ቤትህ የመጣውን እምርልኃለው አንተ ከገባህበት ገነት መንግስተ ሰማያት አገባዋለሁ አለው፤ አባታችንም “አቤቱ ጌታ ሆይ የኢትዮጰያን ህዝብ ማርልኝ” አለው፤ እነሆ ምሬልኃለው አስራት በኩራት አድርጌም ሰጥቼሃለው፤ ከመጋቢት አምስት ቀን ጀምሮ ዝክርህን ያድርጉ በአማላጅነትህም ይማጸኑ አለው። ከዚህ በኃላ ሰባቱ ሊቃነ መላክት የአባታችንን ነፍስ ሊቀበሉ ወረዱ በታላቅ ምስጋናም ወደ ሰማይ አሳረጉት ስጋውንም ይዘውት ሄዱ የት እንደተቀበረ ግን እስካሁን አይታወቅም አንዳንዱ በእየሩሳሌም ነው ይላሉ፤ ሌላው በምድረ ከብድ ነው ይላል ግን እስካሁን ልክ እንደ ሊቀ ነብያት ሙሴ ስጋ የት እንደተቀበረ አይታወቅም። ገድሉ ትሩፋቱ ከሰማይ ከዋክብት ከምድር አሸዋ ይበዛል ኢትዮጰያን አብዝቶ ይወዳታል፤ ምድራዊ ምግብ አልተመገበም የእናቱን ጡት እንኳን አልጠባም፤ ልብስ፤ መጠለያ አልፈለገም፤ የክረምት ቁር የበጋ ሐሩር እየተፈራረቀበት በተጋድሎ 562 ዓመት ኖረ፤ በዛሬዋ ቀን ሩጫውን ጨረሰ። ለእግዚያብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም ከአባታችን በረከት ያሳትፈን። ታሪክ:- አዲስ አበባ የሚገኘው ሳሪስ አቦ ቤተክርስቲያን ከዕለታት በአንዱ ቀን ጻደቁ አባታችን ወደ ዝቋላ ሲሄዶ ለጥቂት ቀናት ቦታው ላይ አርፈውበት እንደነበር ይነገራል፤ይህ ከሊቃውንቱ አንደበት ያገኘነው ቃል ነው።http://delateasmelash.blogspot.no/


                           “ዝክረ ጻድቅ ለዓለም ይሄሉ፡፡”

         በመስአበ ወወልድ ወንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን   
እግዚአብሔር የቅዱሳንን ነፍስ ይጠብቃል ከሃጢአት እጅም ያድናቸዋ፡፡ መዝ.96፡10
ታላቁ ጻድቅ አቡነ ሀብተማርያም የተወለዱት በመንዝ አውራጃ ልዩ ስሙ የራዊ በተባለ ቦታ ሲሆን የአባታቸው ስም ፍሬ ብሩክ የእናታቸው ስም ዮስቴና ይባላል፡፡ ሁለቱም በሕግ ጋብቻ ጸንተው ሕገ እግዚአብሔርን ጠብቀው ምግባር ቱሩፋት ሰርተው በስጽህና በቅድስና ይኖሩ ነበር፡፡ ሆኖም ልጅ አለነበራቸውም፡፡ ቢህ ሁኔታ ያዘኑ ቅድስት ዮስቴና ማለት እናታቸው መንነው በአከባቢያቸው ከሚገኝ ጫካ ውስጥ ዋሻ ፈልገው ገብተው ዘጉ፡፡ በዚያም አንድ መናኝ መነኩሴ አግኝተዋቸው እግዚአብሔር በቅድስቲቱ ያለው ድብቅ ነገር ስለገለጠላቸው አንቺ ለምንኩስና የተፈቀደልሽ አይደለሽም ወደ ቤትሽ ግቢ ጸሎቱ ለዓለም ሁሉ የሚጠቅም ሰው ሁሉ የሚማጸነው ስሙ፣ ገድሉ ትሩፋቱ በዓለም ሁሉ የሚነገርለት ወንድ ልጅ ትወልጃለሽ አሏቸው፡፡ የእግዚአብሔርን ድንቅ ተዓምር የሰሙ ቅድስት ዮስቴናም እግዚአብሔርን እያመሰገኑ ወደ ቤቸው ተመለሱ፡፡ የተናገረውን የማያስቀር አምላክ በቸርነቱ ጎበኛቸውና ነሃሴ 26 ቀን ጸነሱ፡፡

ግንቦት 26 ቀንም ደም ግባታች እንደ ንጋት ኮከብ ያማሩ ሃብተማርያም ተወለዱ፡፡ እግዚአብሔር ለቅድስና ሥራ ስለመረጣቸው በእናተቸው ጀርባ ታዝለው ወደ ቤተክርስቲያን ሄደው በሕጻን አንደበታቸው ከቀዳሹ ካህን ጋር “እግዚኦ ማሐረነ ክርስቶስ” በማለት ይጸልዩ ነበር፡፡ ባደጉም ጊዜ ይህን ጸሎት ደጋግመው ይጸልዩ ነበር፡፡ ላባቸውም እስኪንጠባጠብ ድረስ በመስገድ ይጋደሉ ነበር፡፡ አንድ ቀንም ከአባታቸው ጎን እንደ ተኙ በድንገት እግዚአብሔር በድምጽ “ሀብተማርያም ሆይ! አንተን የተመረጠ ዕቃ አድርጌሃለሁና ቃሌን ለተመረጡ ሰዎች ተናገር” አላቸው፡፡ ይህን ግን የተበሰረላቸው የቤተሰቦቻቸውን ከብቶች በሚጠብቁበት ጊዜ ነበር፡፡ እድሜያቸው እየገፋ ሲሄድ አባታቸው ትምህርት ቤት አስገቡአቸው፡፡ ለአቅመ አዳም በደረሱ ጊዜ ሚስት አጩላቸው፤ እርሳቸው ግን የድንግልናን ህይወት በመምረጥ ከወላጃቸው ቤት ኮብልለው ገዳም ገቡ፡፡ ” ልጄ ሆይ እራስህንለእግዚአብሔር ታስገዛ ዘንድ ወደ ገዳም ብትሄድ ሰውነትህ ለመከራ አዘጋጅ፡፡” በዚያን አባ ሳሙኤል ለሚባሉ በረዳትነት ሲያገለግሉብዙ ገቢረ ተዓምራት ተደርጎላቸዋል፡፡  
ዛሬ ይሰበይ ገዳም ተብሎ በሚጠራው ሥፍራ ለሦስት ወራት ጽሙድ እንደበሬ ትጉህ እንደ ገበሬ እንዲሉ በጾም በጸሎት ተጠምደው ሳለ መታሰቢያህን በዚህ ዋሻ አደርግልሃለሁ በማለት እግዚአብሔር ቃል ኪዳን ገብቶላቸዋል፡፡ ይህም ዋሻ የይሰበይአባ ሀብተ ማርያም ገዳም በመባል በሰሜን ሸዋ ሰላሌ አህጉረ ስብከት ከደብረሊባኖስ ወደ ቆላው ዝቅ ብሎ በእግር የ2 ሰዓት መንገድ ላይ ይገኛል፡፡ ገዳሙንም በስማቸው መሠረቱ፡፡ በዓለ ጊዜ እረፍታቸው በደረሰ ጊዜ ጌታ ተገልጦላቸው ስለ ተጋድሎአቸውና ስለንጽህናቸው ሳባት አክሊል እንደሚቀበሉ ነግሯቸዋል፡፡ በ 490 ዓ.ም ህዳር 26 ቀን ዐርፈው በደብረሊባኖስ ገዳም መካነ ቅዱሳን ቀበሯቸው፡፡



+++++ምግባሩ የተወደደ የሆነ የጸድቁ ባህታዊ ብስራት የተጸነስክበት የእናት የዮስቴና ማህጸን በእውነት ሰላምታ ይገባል፡፡ ጻድቁ አባቴ ሆይ ሀብተማርያም እንደዮና ልጅ እንደ ጴጥሮስ የእውነት ሥራን አስተምረኝ አይነ ልቦናዬንም አብራልኝ ፍጽምት ከሆነች ትህትና ጋር ባልንጀራኤን እንደራሴ እወድ ዘንድ፡፡
ሰላም ለዝክረ ስምክ፡- በዃለኛው ዘመን የዚህን ዓለም ረሃብና ጥም የሚያስረሳና ከወይን ዘለላ ይልቅ ለሚወደድ ስም አጠራርህ ሰላምታ ይገባል፡፡ ህጻን የሆነ የማርያም ልጅ ወዳጅ ጻድቁ አባቴ አቡነ ሀብተ ማርያም ሆይ በቦታው ታርፍለት ዘንድ ጻድቁ አባታችን አቡነ ተክለ ሃይማኖት አጥብቆ እንደ ለመነ እኔም አገልጋይ ከሀዘን ሁሉ ታድነኝና በቤቴም ታርፍ ዘንድ እለምነሃለሁ፡፡+++++
 ምንጭ ነገረ ቅዱሳን፣መልክአ አቡነ ሀብተማርያም እና ሐመር መጽሔት 4ኛ ዓመት ቁጥር 3 የአባታችን የጻድቁ አቡነ ሀብተማርያም ረድኤት፣ በረከት፣ ምልጃና ቃል ኪዳናቸው አይለየን፡፡ካለመኖር ወደ መኖር ያመጣኝ፣ ካለማወቅ ወደ መረዳት ያደረሰኝ አነሳስቶ ላስጀመረኝ አስጀምሮ ላስፈጸመኝ ጥንት ላሌለው ቀዳማዊ ፍጻሜ ላሌለው ድህራዊ ያልኖረበት ጊዜ የሌለ የማይኖርበት ጊዜም የማይኖር የዘላለም ንጉስ ሁሉን ቻይ ፈጣሪ እግዚአብሔርን በራስ ፀጉሬ ቁትርበአጥንቶቼም ልክ አመሰግናለሁ፡፡ 




                                    ሊቀ  ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስ

                                                 
የቅዱስ ጊዮርጊስ አባት መስፍን ነው ስሙም ዞሮንቶስ (አናስጣስዮስ) ይባላል እናቱም ቴዎብስታ ትባላለች በህጻንነቱም አባቱ አረፈ
20 ዓመት ሲሆነው የ አባቱን ሹመት ሊቀበል ወደ ምጉስ ዱድያኖስ ሔደ ኑጉሱም ጣዖት አቁኖ ጣዖትን እንዲያመልኩ ሰወቸን ሁሉ
ሲያስገድዳቸው አገኘው ይህንንም አይቶ ቅዱስ ጊዮርጊስ እጅግ አዘነ በእርሱም ዘንድ ያለውን ገንዘቡን ሁሉ ለድሆች ለምስጊኖች ሰጠ ባሮችንም ነጻ አወጣቸው  ከዚህም በሁዋላ በንጉስ ፊት ቆመ በክብር ባቤት በኢየሱስ ክርስቶስ ታመነ ንጉስ ግን እንዲክድ አባበለው ብዙ ቃልኪዳንመ ገባለት እርሱ ግን አልተቀበለውም ንጉስም ባለመታዘዙና ባለመመለሱ እጀግ አዘነ ስለዚህም አትናትዮስ የ ሚባላ ታላቅ ስራይኛ አመጣ ዕርሱም ምርዝን ቀምሞ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ሰጠው እርሱም ጠጣው ነገር ግን ምንም አልጎዳውም መሰርይም በእግዚአብሔር ስም አምኖ በሰማእትነት ሞተ ከ እርሱም ጋር 30700 ሰወች ሰማእትነትን ተቀበሉ

ቅዱስ ጊዮርጊስም ብዙ ተአምራትን እየሰራ አሳፈራቸው እነርሱም በጉድጓድ ብረት ምጣድ ወስጥ አቃጥለው አሳርረውም ስጋና አጥንቱን ፈጭተው አመድ አድርገው ከረጅም ተራራ ላይ በተኑት ጌታችንም አስነሳው እርሱም ተመልሶ የ አማላኩን ስም በ ነገስታቱ ፊት ሰበከ
ነገስታቱም ደግመው ሙታንን ካስነሳህ በአንተአማላክ እናምናለን አሉት እረሱም ጸለየ አስነሳቸውም እንረሱም መሰከሩ ነገስታቱ ግን የ ረቀቁ ሰይጣናት እንጂ ሰወችን አላስነሳህም አሉት
ከዚህም በሑዋላ ንጉሱ ሰማዕቱን አስገረፈው በመንኮራኩርም አበራዩት ሙቶም ከከተማ ውጭ ጣሉት ጌታማ ዳግም አስነሳው ወደነገስታቱም ተመለሰ ከዝህም በሁዋላ ንጉስ ይሸነግለው ዘንድ ጀመረ በመንግስቱ ላይም ሁለተኛ ሊያደርገው ቃል ገባለት ቅዱሱም ነገ ጥዋት ለ አማልክቶችህ መስዋእት አቀርባለሁ አንተም ህዝቦች እንዲሰበሰቡ እዘዝ አለው ንጉሱም ደስ አለው አደረገም
ሰውም ተሰበሰበ ቅዱስ ጊዮርጊስም በእግዚአብሔር ስም አጵሎን የተባለውን ጣዖት ወደርሱ እነዲመጣ አዘዘው ጣዖቱም እኔ ሰውን የማስት እንጅ አማላክ አይደለሁም አለ ምድርም ዋጠችው ጣዖታቱም ተሰባበሩ ንጉስም አፈረ
ንጉሱም ቅዱስ ጊዮርጊስ ራስ እንዲቆረጥ አዘዘ እርሱም ደስ አለው ጌታችንም ለስማዕቱ ብዙ ቃል ኪዳንን ገባለት በሰይፈም ተቆረጠ የ ሰማዕትነትን አክሊልንም ተቀበለ
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን የቅዱስ ጊወርጊስ በረከት ረድኤቱ ከሁላችን ጋር ይሁን ከስጋን ከነፍስ መከራ ይጠብቀን ለዘላለሙ አሜን



 

No comments:

Post a Comment