ጥቅስ

ጌታዬ
እግዚአብሔር ሆይ
እስከዚህ ያደረስኸኝ
እኔ ማን ነኝ ?
ቤቴስ ምንድር ነው?
2 ሳሙ 7፥18

Tuesday 16 October 2012

ብፁእ አባታችን አቡነ ዘርዐ ቡሩክ


በረከታቸዉ ይደርብንና ብፁእ አባታችን አቡነ ዘርዐ ቡሩክ ከአባታቸዉ ከቅዱስ ደመ ክርስቶስ ከናታቸዉ ከቅድስት ማርያም ሞገሳ 8 ኛዉ መቶ /ዘመን መጨረሻ በክብር ተወለዱ ከመወለዳቸዉ አስቀድሞ ቅድመ አያታቸዉ ከኔ ዘር 7 ትዉልድ አንዲት ሴት ትወልዳለች ከርሶም አለምን በጸሎቱ የሚያድን ይወለዳል ብለዉ ትቢት ተናግረዉላቸዉ ነበር፡፡ በተወለዱ 7 አመታቸዉ ይህን አለም ክፋቱን እንዳላይ አይኖቸን አሳዉርልኝ ብለዉ ጸለዪ አይኖቻቸዉም እስከ 12 አመታቸዉ ማየት አይችሉም ነበር፡፡ ከዛም በኋላ የዓለምን ክብር በመናቅ በትምህርት ምክንያት ከሃገር ወደ ሃገር ከገዳም ደ ገዳም እየተዘዋወሩ ብዙ ታምራትን ሲያደርጉ ቆይተዋል፡፡ ከአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ጋር መጋቢት 27 ቀን ዲያቆን ሆነዉ ቀድሰዋል ፤ በአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሞት ጊዜም ተገኝተዋል በአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገድል መጽሃፍ ላይም ሰፍረዉ ይገኛሉ 12 ክንፎችም ተሰተዋቸዋል በግዮን ምንጭ ግሽ አባይ በተባለዉ ቦታ 30 አመታት ጸልየዋል አሁንም በዛዉ ግሺ አባይ ፈለገ ግዮን ቅዱስ ሚካኤል እና አቡነ ዘርአ ቡሩክ ቤተክርስቲያን በጸበላቸዉ ታምራት እየተደረገ ነዉ ፡፡
ታህሳስ 13 አባታችን አቡነ ዘርዐ ቡሩክን የምናስብበት ቀን ነዉ ከበረከታቸዉ ያካፍለን አሜን
ምንጭ : ገድለ ዘርዐ ቡሩክ እና ተአመረ ዘርዐ ቡሩክ በግዕዝና በአማርኛ
ይህ የምታዪት ደብር ፈለገ ግዮን ግሽ አባይ አቡነ ዘርዐ ቡሩክ እና የቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ነዉ።

1 comment: