ጥቅስ

ጌታዬ
እግዚአብሔር ሆይ
እስከዚህ ያደረስኸኝ
እኔ ማን ነኝ ?
ቤቴስ ምንድር ነው?
2 ሳሙ 7፥18

Thursday 11 October 2012

ሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስ

                                                ሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስ


የቅዱስ ጊዮርጊስ አባት መስፍን ነው ስሙም ዞሮንቶስ (አናስጣስዮስ) ይባላል እናቱም ቴዎብስታ ትባላለች በህጻንነቱም አባቱ አረፈ
20 ዓመት ሲሆነው የ አባቱን ሹመት ሊቀበል ወደ ምጉስ ዱድያኖስ ሔደ ኑጉሱም ጣዖት አቁኖ ጣዖትን እንዲያመልኩ ሰወቸን ሁሉ
ሲያስገድዳቸው አገኘው ይህንንም አይቶ ቅዱስ ጊዮርጊስ እጅግ አዘነ በእርሱም ዘንድ ያለውን ገንዘቡን ሁሉ ለድሆች ለምስጊኖች ሰጠ ባሮችንም ነጻ አወጣቸው ከዚህም በሁዋላ በንጉስ ፊት ቆመ በክብር ባቤት በኢየሱስ ክርስቶስ ታመነ ንጉስ ግን እንዲክድ አባበለው ብዙ ቃልኪዳንመ ገባለት እርሱ ግን አልተቀበለውም ንጉስም ባለመታዘዙና ባለመመለሱ እጀግ አዘነ ስለዚህም አትናትዮስ የ ሚባላ ታላቅ ስራይኛ አመጣ ዕርሱም ምርዝን ቀምሞ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ሰጠው እርሱም ጠጣው ነገር ግን ምንም አልጎዳውም መሰርይም በእግዚአብሔር ስም አምኖ በሰማእትነት ሞተ ከ እርሱም ጋር 30700 ሰወች ሰማእትነትን ተቀበሉ


ቅዱስ ጊዮርጊስም ብዙ ተአምራትን እየሰራ አሳፈራቸው እነርሱም በጉድጓድ ብረት ምጣድ ወስጥ አቃጥለው አሳርረውም ስጋና አጥንቱን ፈጭተው አመድ አድርገው ከረጅም ተራራ ላይ በተኑት ጌታችንም አስነሳው እርሱም ተመልሶ የ አማላኩን ስም በ ነገስታቱ ፊት ሰበከ
ነገስታቱም ደግመው ሙታንን ካስነሳህ በአንተአማላክ እናምናለን አሉት እረሱም ጸለየ አስነሳቸውም እንረሱም መሰከሩ ነገስታቱ ግን የ ረቀቁ ሰይጣናት እንጂ ሰወችን አላስነሳህም አሉት
ከዚህም በሑዋላ ንጉሱ ሰማዕቱን አስገረፈው በመንኮራኩርም አበራዩት ሙቶም ከከተማ ውጭ ጣሉት ጌታማ ዳግም አስነሳው ወደነገስታቱም ተመለሰ ከዝህም በሁዋላ ንጉስ ይሸነግለው ዘንድ ጀመረ በመንግስቱ ላይም ሁለተኛ ሊያደርገው ቃል ገባለት ቅዱሱም ነገ ጥዋት ለ አማልክቶችህ መስዋእት አቀርባለሁ አንተም ህዝቦች እንዲሰበሰቡ እዘዝ አለው ንጉሱም ደስ አለው አደረገም
ሰውም ተሰበሰበ ቅዱስ ጊዮርጊስም በእግዚአብሔር ስም አጵሎን የተባለውን ጣዖት ወደርሱ እነዲመጣ አዘዘው ጣዖቱም እኔ ሰውን የማስት እንጅ አማላክ አይደለሁም አለ ምድርም ዋጠችው ጣዖታቱም ተሰባበሩ ንጉስም አፈረ
ንጉሱም ቅዱስ ጊዮርጊስ ራስ እንዲቆረጥ አዘዘ እርሱም ደስ አለው ጌታችንም ለስማዕቱ ብዙ ቃል ኪዳንን ገባለት በሰይፈም ተቆረጠ የ ሰማዕትነትን አክሊልንም ተቀበለ
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን የቅዱስ ጊወርጊስ በረከት ረድኤቱ ከሁላችን ጋር ይሁን ከስጋን ከነፍስ መከራ ይጠብቀን ለዘላለሙ አሜን


No comments:

Post a Comment