ጥቅስ

ጌታዬ
እግዚአብሔር ሆይ
እስከዚህ ያደረስኸኝ
እኔ ማን ነኝ ?
ቤቴስ ምንድር ነው?
2 ሳሙ 7፥18

Saturday 6 October 2012

አቡነ ሀብተማርያም

“ዝክረ ጻድቅ ለዓለም ይሄሉ፡፡” በመስአበ ወወልድ ወንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

እግዚአብሔር የቅዱሳንን ነፍስ ይጠብቃል ከሃጢአት እጅም ያድናቸዋ፡፡ መዝ.96፡10
ታላቁ ጻድቅ አቡነ ሀብተማርያም የተወለዱት በመንዝ አውራጃ ልዩ ስሙ የራዊ በተባለ ቦታ ሲሆን የአባታቸው ስም ፍሬ ብሩክ የእናታቸው ስም ዮስቴና ይባላል፡፡ ሁለቱም በሕግ ጋብቻ ጸንተው ሕገ እግዚአብሔርን ጠብቀው ምግባር ቱሩፋት ሰርተው በስጽህና በቅድስና ይኖሩ ነበር፡፡ ሆኖም ልጅ አለነበራቸውም፡፡ ቢህ ሁኔታ ያዘኑ ቅድስት ዮስቴና ማለት እናታቸው መንነው በአከባቢያቸው ከሚገኝ ጫካ ውስጥ ዋሻ ፈልገው ገብተው ዘጉ፡፡ በዚያም አንድ መናኝ መነኩሴ አግኝተዋቸው እግዚአብሔር በቅድስቲቱ ያለው ድብቅ ነገር ስለገለጠላቸው አንቺ ለምንኩስና የተፈቀደልሽ አይደለሽም ወደ ቤትሽ ግቢ ጸሎቱ ለዓለም ሁሉ የሚጠቅም ሰው ሁሉ የሚማጸነው ስሙ፣ ገድሉ ትሩፋቱ በዓለም ሁሉ የሚነገርለት ወንድ ልጅ ትወልጃለሽ አሏቸው፡፡ የእግዚአብሔርን ድንቅ ተዓምር የሰሙ ቅድስት ዮስቴናም እግዚአብሔርን እያመሰገኑ ወደ ቤቸው ተመለሱ፡፡ የተናገረውን የማያስቀር አምላክ በቸርነቱ ጎበኛቸውና ነሃሴ 26 ቀን ጸነሱ፡፡
ግንቦት 26 ቀንም ደም ግባታች እንደ ንጋት ኮከብ ያማሩ ሃብተማርያም ተወለዱ፡፡ እግዚአብሔር ለቅድስና ሥራ ስለመረጣቸው በእናተቸው ጀርባ ታዝለው ወደ ቤተክርስቲያን ሄደው በሕጻን አንደበታቸው ከቀዳሹ ካህን ጋር “እግዚኦ ማሐረነ ክርስቶስ” በማለት ይጸልዩ ነበር፡፡ ባደጉም ጊዜ ይህን ጸሎት ደጋግመው ይጸልዩ ነበር፡፡ ላባቸውም እስኪንጠባጠብ ድረስ በመስገድ ይጋደሉ ነበር፡፡ አንድ ቀንም ከአባታቸው ጎን እንደ ተኙ በድንገት እግዚአብሔር በድምጽ “ሀብተማርያም ሆይ! አንተን የተመረጠ ዕቃ አድርጌሃለሁና ቃሌን ለተመረጡ ሰዎች ተናገር” አላቸው፡፡ ይህን ግን የተበሰረላቸው የቤተሰቦቻቸውን ከብቶች በሚጠብቁበት ጊዜ ነበር፡፡ እድሜያቸው እየገፋ ሲሄድ አባታቸው ትምህርት ቤት አስገቡአቸው፡፡ ለአቅመ አዳም በደረሱ ጊዜ ሚስት አጩላቸው፤ እርሳቸው ግን የድንግልናን ህይወት በመምረጥ ከወላጃቸው ቤት ኮብልለው ገዳም ገቡ፡፡ ” ልጄ ሆይ እራስህንለእግዚአብሔር ታስገዛ ዘንድ ወደ ገዳም ብትሄድ ሰውነትህ ለመከራ አዘጋጅ፡፡” በዚያን አባ ሳሙኤል ለሚባሉ በረዳትነት ሲያገለግሉብዙ ገቢረ ተዓምራት ተደርጎላቸዋል፡፡
ዛሬ ይሰበይ ገዳም ተብሎ በሚጠራው ሥፍራ ለሦስት ወራት ጽሙድ እንደበሬ ትጉህ እንደ ገበሬ እንዲሉ በጾም በጸሎት ተጠምደው ሳለ መታሰቢያህን በዚህ ዋሻ አደርግልሃለሁ በማለት እግዚአብሔር ቃል ኪዳን ገብቶላቸዋል፡፡ ይህም ዋሻ የይሰበይአባ ሀብተ ማርያም ገዳም በመባል በሰሜን ሸዋ ሰላሌ አህጉረ ስብከት ከደብረሊባኖስ ወደ ቆላው ዝቅ ብሎ በእግር የ2 ሰዓት መንገድ ላይ ይገኛል፡፡ ገዳሙንም በስማቸው መሠረቱ፡፡ በዓለ ጊዜ እረፍታቸው በደረሰ ጊዜ ጌታ ተገልጦላቸው ስለ ተጋድሎአቸውና ስለንጽህናቸው ሳባት አክሊል እንደሚቀበሉ ነግሯቸዋል፡፡ በ 490 ዓ.ም ህዳር 26 ቀን ዐርፈው በደብረሊባኖስ ገዳም መካነ ቅዱሳን ቀበሯቸው፡፡

+++++ምግባሩ የተወደደ የሆነ የጸድቁ ባህታዊ ብስራት የተጸነስክበት የእናት የዮስቴና ማህጸን በእውነት ሰላምታ ይገባል፡፡ ጻድቁ አባቴ ሆይ ሀብተማርያም እንደዮና ልጅ እንደ ጴጥሮስ የእውነት ሥራን አስተምረኝ አይነ ልቦናዬንም አብራልኝ ፍጽምት ከሆነች ትህትና ጋር ባልንጀራኤን እንደራሴ እወድ ዘንድ፡፡
ሰላም ለዝክረ ስምክ፡- በዃለኛው ዘመን የዚህን ዓለም ረሃብና ጥም የሚያስረሳና ከወይን ዘለላ ይልቅ ለሚወደድ ስም አጠራርህ ሰላምታ ይገባል፡፡ ህጻን የሆነ የማርያም ልጅ ወዳጅ ጻድቁ አባቴ አቡነ ሀብተ ማርያም ሆይ በቦታው ታርፍለት ዘንድ ጻድቁ አባታችን አቡነ ተክለ ሃይማኖት አጥብቆ እንደ ለመነ እኔም አገልጋይ ከሀዘን ሁሉ ታድነኝና በቤቴም ታርፍ ዘንድ እለምነሃለሁ፡፡+++++
ምንጭ ነገረ ቅዱሳን፣መልክአ አቡነ ሀብተማርያም እና ሐመር መጽሔት 4ኛ ዓመት ቁጥር 3 የአባታችን የጻድቁ አቡነ ሀብተማርያም ረድኤት፣ በረከት፣ ምልጃና ቃል ኪዳናቸው አይለየን፡፡ካለመኖር ወደ መኖር ያመጣኝ፣ ካለማወቅ ወደ መረዳት ያደረሰኝ አነሳስቶ ላስጀመረኝ አስጀምሮ ላስፈጸመኝ ጥንት ላሌለው ቀዳማዊ ፍጻሜ ላሌለው ድህራዊ ያልኖረበት ጊዜ የሌለ የማይኖርበት ጊዜም የማይኖር የዘላለም ንጉስ ሁሉን ቻይ ፈጣሪ እግዚአብሔርን በራስ ፀጉሬ ቁትርበአጥንቶቼም ልክ አመሰግናለሁ፡፡
 

No comments:

Post a Comment