ጥቅስ

ጌታዬ
እግዚአብሔር ሆይ
እስከዚህ ያደረስኸኝ
እኔ ማን ነኝ ?
ቤቴስ ምንድር ነው?
2 ሳሙ 7፥18

Sunday 30 September 2012

እንኳን ለ ግሸን ማርያም ታላቅ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ !

 

እንኳን ለንጽሕተ ንጹሓን ቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም ወላዲተ አምላክ ግሸን ደብረከርቤ ዳግማዊት ጎልጎታ - የግማደ መስቀሉ መገኛ ♥†♥†♥† ታላቅ ክብረ በዓል አደረሳችሁ!!!!

✙ ✙ ✙ ግማደ መስቀሉ ከጎሎጎታ እስከ ግሸን ደብረ ከርቤ ✙ ✙ ✙

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሞት በስላጣኑ ከተነሳ በሗላ መስቀሉ ቀን ከማታ ያበራ ነበረ። አይሁድ ቀንተው ቀበሩትና የቆሻሻ መጣያ እንዲሆን አወጁ። ከ300 ዘመን በሗላ የንጉስ ቆስጠንጢኖስ እናት ንግስት እሌኒ ከቁስጥንጥኒያ መታ የክርስቶስን መስቀል አስቆፍራ ለማውጣት በጸሎት 7 ቀን ከቆየች በሗላ መላኩ ዑራኤል ተገልጾ ደመራ አስደምረሽ በእሳት አያይዘሽ በዛ ላይ ብዙ እጣን አድርጊ የእጣኑ ጢስ ወደ ላይ ወቶ መስቀሉ ያለበትን ቦታ ያሳይሻል አላት። እንዳላትም አድርጋ መስከረም 10 ቀን 370 ዓ.ም ሃይላችን የሆነው መስቀሉ ተገኘ።


መስቀሉ ቀንና ለሊታ ሲያበራ የፋርስ ባቢሎን ንጉስ ወደ ሃገሩ ወሰደው። በዚህም ግዜ የእየሩሳሌም ንጉስ ለሮማው ለንጉስ እርቃን እርዳታ ጠየቀ። የሮማው ንጉስ ዳግመኛ መስቀሉን በሃገሬ አኖራለሁ ብሎ ወደ እየሩሳሌም ዘመተ። በዚህን ግዜ የእየሩሳሌም ንጉስ የፋርስን ንሱስ ረዳት አድርጎ ሲከላከል የ4ቱ ክፍላተ አለም የሃይማኖት አባቶች መስቀሉ ለ4 ተከፍሎ በ4ቱ ሃያለን መንግስታት ቢቀመጥ ይሻላል አሉ። የቀኝ እጁ ያረፈበት ግማደ መስቀሉ ለአፍሪካ ደረሰ። አፍሪካዊያን ተማክረው ግብጽ እስክንድርያ ገዳም ውስጥ እንዲቀመጥ አደረጉ።

✙ ግማደ መስቀሉ ወደ ግሸን ደብረ ከርቤ ✙

የግብጽ እስላሞች በብዛትና በሃይላቸው ባየሉ ግዜ የእስክንድርያን ክርስቲያኖች አስጨነቁ። አባ ሚካኤልና አባ ገብርኤል የሚባሉ ሁለት የግብጽ ጳጳሳትን አሰሩ።
በዚህን ግዜ የግብጽ ክርስቲያኖች በወቅቱ ሃያል ለነበረው ለኢትዮጲያ ንጉስ ከአፄ ዳዊት እርዳታን ጠየቁ። ንጉስ አፄ ዳዊትም መነኮሳትን ባህታዊያንንና ካህናትን ሰብስቦ በጉባኤ ውሳኔ ወሰኑ ፦ ሁለቱ ጳጳሳት እንዲፈቱና የግብጽ ክርስቲያኖች የግፍ አገዛዝ እንዲቆም የክርስቶስ መስቀልም ወደ ኢትዮጲያ እንዲመጣ ብለው ታላቁን ጉባኤ ፈጸሙ። ንጉስ አፄ ዳዊት በ10ሺ ፈረሰኞች በ10ሺ በቅሎ በ10ሺ ግመልና በብዙ እግረኞች ታጅበው ወደ ስናር (ካርቱም) ደረሱና መልእክት ወደ ግብጽ ላኩ። የተሰጣቸውን የወርቅ ስጦታ መልሰው ግማደ መስቀሉን ከብዙ ቅዱሳን አጽም ጋር ጠይቀው ተሰጣቸው። በስም አጠራር አንድ የሆኑት ሁለቱ ንጉሶች (ልበ አምላክ ዳዊት ና አፄ ዳዊት) በተግባርም አንድ የሚያደርጋቸር ስራ አለ ፦ ልበ አምላክ ዳዊት ታቦተ ጺዮንን አጅቦ እንደዘመረው ሁሉ ንጉስ አፄ ዳዊትም በእጁ እያጨበጨበ በግምባሩ እየሰገደ ግማደ መስቀሉን ተቀበለ። በእንዲህ እንዳለ ንጉሱ በድንገት ስናር በተባለ ቦታ በቅሎ ረግጧቸው አረፉ። በምትካቸው የኢትዮጲያ ፈላስፋ በመባል የሚያወቁት ንጉስ ዘረያቆብ ነገሱ። ንጉስ ዘረያቆብ በነገሱ በ15 አመታቸው እግዚአብሔር በራዕይ ታያቸውና “መስቀሌን በመስቀለኛው አምባ ላይ አድርግ” የሚል ራዕይ አዩ። ንጉስ ዘረያቆብ 3 አመት በጾም በጸሎት መስቀለኛው ቦታ እንዲገለጽለት ጠየቀ።
♥ መላዕኩ ዑራኤል♥ መስቀለኛው ቦታ ግሸን ደብረ ከርቤ እንደሆነ አሳየው
ንጉስ ዘረያዕቆብም ግማደ መስቀሉን
በግሸን ደብረ ከርቤ አኖረው።
የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት እና ተራዳኢነት ከሁላችን ጋር ይሁን።
የጌቶች ጌታ የንጉሶች ንጉስ ልዑል እግዚአብሔር ዛሬም ዘወትርም ስሙ የተመሰገነ ይሁን።አሜን አሜን አሜን !!! —
 
 

No comments:

Post a Comment