ጥቅስ

ጌታዬ
እግዚአብሔር ሆይ
እስከዚህ ያደረስኸኝ
እኔ ማን ነኝ ?
ቤቴስ ምንድር ነው?
2 ሳሙ 7፥18

Wednesday 26 September 2012

አቡነ እሰትነፋሰ ክርሰቶሰ

እሰትነፋሰ ክርሰቶሰ  አባቱ መላከ ወለተ ማርያም የባላሉ።በመጀመሪያም መላኩ መጥቶ ለናቱ መልካም ልጅ እንደምትወልድ ነገራት። አገሩ ዳውንት ደላነታ አውራጃ ሲሆን በ24 አመቱ መነኮሰ ገዳሙን አቡነ አትናቲዎሰ አድሰወታል። ይህ ገዳም እጅግ ባለ ታሪክ ነው የተመረጠ በመሆኑ በመላእክት የተመሰከረለት ከአደገ በኃላም በሶሰት አመቱ ወደ ሐይቅ እሰቲፋኖሰ ገዳም ገበቶ ያገለገለ የተማረ ነው።ወደ ሐይቅም ሲደረሱ የሚያሻግረው ሲያጣ መልአኩ ደንገል ያቀረበለትና በዚያተሻግሮ ወደ ገዳሙ የገባ ሲጸልይም አቡነ አረጋዊና አጼ ገበረ መስቀል ቅዱሰ ያሬድ  ተገልጸው ያነጋገሩት አባት ነው።
በዚህ በራሱ ገዳም በአሰጂ ከበረሃ ላይ ውሀ አፍልቆ ተማሪዎቹን ያጠጣ ጻድቅ ነው።ያም ፀበል ዛሬ ህሙም ፈዋሸ ሆኖ የሚገኝ ነው። ጻዲቁ በአርማኒያ በዝቋላ በኢየሩሳሌም  በሽዋ በግብጽ ተመላልሷል።
ይህ ጻድቅ በታማኝነቱ ተመርጦ ከንጉሱ ተልኮ የንጉሱን ልጅ የጎንደሩን ጻድቁ ዮሐንሰን እያሰተማረ ያሳደገ ነው።በዚህ ገዳም በቅሎዎች ናቸው የ 9 ሰዓት መንገድ ሄደው ወርደው ከበሸሎ ወንዝ ውሃ መንገደኛው ቀድቶ ሲጭናቸው ሳያጋድሉ የ 9  ሰዓት ምላሽ መንገድ ተጉዘው ከገዳሙ ይገባሉ። ይህ ለጻድቁ የተሰጠ ቃል ኪዳን ነው። የጻድቁን ገዳም የቆረቆረውና የተከለው አቡነ ቤዛ ወልድ የተባለው ጻድቅ ነው። የጻድቁም እረፍት በሚያዝያ ፱ ቀን ከአቡነ ማርቆሰ ግበጻዊ ቅሰና ቁምሰን ተቀበለ። በየካቲት 9 የመነኮሰበት ቀን ነው።የመነኮሰውም በሐይቅ ገዳም ነው በዚህ ገዳም 11 አመት በሹሁመት አገልግሏል። በሰሙም ሁለት ቤተ ክርሰቲያን ተተክለዋል።ወር በገባ በ 9 የአቡነ እሰትነፋሰ ክርሰቶሰ መታሰቢያ ነው የጻድቁ አባታችን የአቡነ እሰትነፋሰ ክርሰቶሰ በረከት በሁላች ላይ ይደር አሜን !!!!!!

No comments:

Post a Comment