ጥቅስ

ጌታዬ
እግዚአብሔር ሆይ
እስከዚህ ያደረስኸኝ
እኔ ማን ነኝ ?
ቤቴስ ምንድር ነው?
2 ሳሙ 7፥18

Thursday, 8 November 2012

ሐዋርያው ቅዱስ ማርቆስ

                                ሐዋርያው ቅዱስ ማርቆስ
ጥቅምት 30 ቀን ሐዋርያው ቅዱስ ማርቆስ የተወለደበት ቀን ነው፤ በመዲናችን አዲስ አበባ ጨምሮ በስሙ በታነጹለት አብያተ ክርስቲያናት ታቦተ ህጉ ወጥቶ በደማቁ ተከብሮ ይውላል፤ ሚያዚያ 30 እረፍቱ ነው። ቅዱስ ማርቆስ ቁጥሩ ከ 72ቱ አርድእት ነው፤ የእናቱ ስም ማርያም ይባላል ቁጥሯ ከ 36ቱ ቅዱሳት አንስት ነው፤ በ 50ኛው ቀን መንፈስ ቅዱስ ለሐዋርያት የወረደላቸው በዚህች ቅድስት እናት ቤት ሆነው ሲጸልዩ ነው፤ ሐዋ 2፤1 12፤12 ፤ ይህ ሐዋርያ ወንጌሉን የጻፈው ጌታ

Tuesday, 6 November 2012

አቡነ መብአ ጽዮን

                 አቡነ መብአ ጽዮን

ጥቅምት 27 ቀን ኢትዮጵያዊው ጻድቅ አቡነ መብአ ጽዮን የእረፍት ቀናቸው ነው፤ ትውልዳቸው ሸዋ ትጉለት ውስጥ ነው:: እመቤታችን ያወጣችላቸው ስም ተክለ ማርያም ነው፤እኚህ ጻድቅ በጣም የሚታወቁበት ተጋድሎ አላቸው፤ ይህም አርብ አርብ ቀን የጌታችንን ሞቱን ለማሰብ ትልቅ ድንጋይ በጀርባቸው አዝለው እልፍ እልፍ እየሰገዱ ማታ ላይ ኮሶ ይጠጡ ነበር፤ ሀሞት መጠጣቱን ለማሰብ፤ ከጽድቃቸው ብዛት የተነሳ መቋሚያቸውን ቢተክሉት ሎሚና ትርንጎ አፈርቷል፤

Sunday, 4 November 2012

አባ ሳሙኤልዘዋልድባ

                        አባ ሳሙኤል ዘዋልድባ



(by Wubishet Tekle )ታሀሳስ 12 በዚህች ቀን ታላቁ ኢትዮጰያዊው ጻድቅ አባ ሳሙኤል አረፈ። የትውልድ ቦታው አክሱም ነው፤ 18 ዓመቱ ከአቡነ መድሐኒነ እግዚ እጅ ምንኩስናን ተቀበለ በዚያው በደብረ ባንኮል 13 ዓመት በተጋድሎ ኖረ፤ከዚያም ወደ ጎንደር ደምቢያ ሄደ 3 ወር ከዘረጋ ሳያጥፍ ከቆመ ሳያርፈ እህል ውኃ ሳይቀምስ በተጋድሎ ኖረ፤ከድካም ብዛት አጥንቱ ተሰብሮ ወደቀ ጌታችን ተገለጸለት አበረታው ያንተ ክፍልህ እዚህ አይደለም ወደ ዋልድባ ሂድ አለው፤ ወደ ዋልድባ ሄደ በዚያም ግርማ ሌሊቱን ድምጸ አራዊቱን ታግሶ ማቅ ለብሶ ድንጋይ ተንተርሶ በተጋድሎ ኖረ። ይህ አባት ለእመቤታችን ልዩ ፍቅር ነበረው ውዳሴዋንና ቅዳሴዋን በቀን 64 64 ጊዜ ይጸልይ ነበር፤ውዳሴዋን እየደገመ መንገድ ሲሄድ ከምድር ክንድ ከስንዝር ከፍ ይላል፤

Sunday, 28 October 2012

አቡነ እየሱስ ሞአ

                            አቡነ እየሱስ ሞአ

ገድለኛው አባ እየሱስ ሞአ ህዳር 26 አረፉ። የተወለዱት ጎንደር ጎርጎራ ልዩ ስሙ ዳህና ሚካኤል በ 1196 ዓ/ም ነው፤ በ 30 ዓመታቸው መንነው ደብረ ዳሞ ሄዱ ፤ በአባ ዮሐኒ እጅ መነኮሱ በተጋድሎም ኖሩ፤ ከዚያም ቅዱስ ገብርኤል እየመራቸው ሐይቅ እስጢፋኖስ መጡ፤ ሐይቅ እስጢፋኖስ ማለት ከደሴ 30 ኪሎ ሜትር ርቆ የሚገኝ ሲሆን የመሰረቱት ካልዕ ሰላማ የተባሉ ግብጻዊ ጻድቅ ናቸው፤ ገዳሙን ከሰሩ በኃላ የማንን ታቦት እናስገባ ብለው ሲያስቡ ቶራ የምትባል እንስሳ ጭነት ተጭና ከመካከላቸው ተገኘች፤ ጭነቱን አውርደው ቢያዩት በሐር ጨርቅ የተጠቀለለ ሁለት ታቦት አገኙ አንዱ የእስጢፋኖስ አንዱ የጊዮርጊስ " ይህንን ታቦት በእየሩሳሌም የሚኖሩ የተሰወሩ ቅዱሳን ከእግዚያብሔር ታዘው የላኩት ነው" የሚል ጽሑፍም አገኙ ይላል።

Friday, 19 October 2012

†♥†አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ†♥†

 †♥†አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ†♥†



“በስመ ሥላሴ”
እግዚአብሔር ያፈቅሮሙ ለጻድቃን እግዚአብሔር የዐቅቦሙ ለፈላስያን፡፡(እግዚአብሔር ጻድቃንን ይወድዳል፤ እግዚአብሔር ስደተኞችን ይጠብቃል፡፡)“ መዝ.፻፵፭፡፰ (145፡8)
አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ

ኢትዮጵያዊው አባት አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ አባቱ መልዓከ ምክሩ እናቱ ወለተ ማርያም ይባላሉ፡፡ የተወለደበት ልዩ ቦታው ወሎ ክፍለ ሀገር ዳውንት ይባላል፡፡ በዚያች ሀገር እግዚአብሔርን የሚፈራ ስሙ መልዓከ ምክሩ የሚባል ደግ ሰው ባለቤቱም ወለተ ማርያም ሁለቱም ደጋጎች እግዚአብሔር እንዳዘዛቸው በእግዚአብሔር ህግ ጸንተው የሚኖሩ መልካም ስራን በመስራት እንደ ዘካርያስና ኤልሳጴጥ እውነተኞች ነበሩ፡፡ሁለት ደጋጎች ልጆችም አሏቸው የተባረከ መልካም ፍሬን የሚያፈራ በመጾም በመጸለይ እግዚአብሔርን የሚያገለግል በጸሎቱ ሰውን የሚጠቅም በጻድቃንም ዘንድ የተመረጠ ልጅ ይሰጣቸው ዘንድ ዘወትር ወደ እግዚአብሔር እና ወደ ድንግል ማርያም ይለምኑ ነበር፡፡
ነብየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት ጆሮውን ወደ ልመናቸው አዘነበለ እንዳለ መዝ 3329 እግዚአብሔር አምላክ በዓይነ ምህረት ተመለከታቸው ልመናቸውንም ሰምቶ አባታችን አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ሚያዚያ 8 ቀን ተጸንሶ ታህሳስ 9 ቀን ተወለደ፡፡ በተወለደ እለትም ተነስቶ በእግሩ ቆሞ 3 ጊዜ ስብሐት ለአብ ስብሐት ለወልድ ስብሐት ለመንፈስ ቅዱስ ብሎ ጣዕም ባለው አንደበቱ ተናገረ፡፡ 9 ጊዜም ህጻናትን ለሚያናግሩ ገዥ ለሚሆኑ ለአጋይዝተ አለምላሴና ለእመቤታችን ለመስቀሉም ሰገደ፡፡ እዚያ ተሰብስበው የነበሩ ብዙ ሰዎች ከህጻኑ አንደበት የስላሴን ምስጋና ሰምተው ፈጽመው አደነቁ ዳግመኛም በዚህ ህጻን ላይ የእግዚአብሔር ጸጋ አድሮበታል ብለው እየተጨዋወቱ ወደ ሀገራቸው ገቡ፡፡