ጥቅስ

ጌታዬ
እግዚአብሔር ሆይ
እስከዚህ ያደረስኸኝ
እኔ ማን ነኝ ?
ቤቴስ ምንድር ነው?
2 ሳሙ 7፥18

Friday 22 February 2013

ጾመ ነነዌ

ጾመ ነነዌ




እግዚአብሔር ነብዩ ዮናስን ወደ ነነዌ ምድር በኃጢአታቸው ምክንያት ሊያመጣው ካሰበው የእሳት ዝናም እንዲትርፉ ቢልከው እግዚአብሔርን ቸርነት ስለሚያውቀው ቸርነትህ ከልክላህ ሳታጠፋቸው ብትቀር እኔ የሐሰት ነቢይ እባል የለምን? ብሎ ሰግቶ ወደ ተርሴስ ሃገር ከነጋዴዎች ጋር ተሳፈረ።
እግዚአብሔርም ታላቅ ማዕበልን አስነሳ በመርከቧ ያሉ ሰዎችም እርስ በራሳቸው ዕጣን ተጣጥለው በዮናስ ላይ ወደቀ። እርሱም ያደረገውን ሰለሚያውቅ ሌሎቹ በውሰጥ ያሉት እንዳይጣል ብዙ ጥረት ቢያደርጉም የግድ መጣል ስለ ነበረበት ወደ ባሕር ተጣለ። እግዚአብሔርም ታላቅ ዓሣ አንበሪን አዘጋጅቶ በከርሠ ዓሣ አንበሪ ሦስት መዓልት ሦስት ሌሊት ቆይቶ በሦስተኛው ቀን በአንጻረ ነነዌ ተፍቶታል። በግድም ቢሆን ስለ ሚመጣባቸው መዓት አስተምሯል። ትንቢተ ዮናስ ምዕራፍ 1 እና 2 ነብዩ ዮናስ ለመጀመርያ ጊዜ ወደ አሕዛብ ሀገር የተላከ ነቢይ ነው።

ዮናስ ማለት ርግብ ማለት ነው። ርግብ የዋህ እንደሆነች እሱም የዋህ ነውና ይህ ቅጽል ተቀጽሎለታል። የርግብ የዋህነት እንደምን ነው ቢሉ በማየ አይኅ (በጥፋት ውሃ )ጊዜ በእባብ አፍ ውስጥ እንቁላል ጥላለች።
ጌታም በወንጌልእንድ ርግብ የዋኃን ሁኑ” ብሎ ተናግሯል። ማቴ 1016 ዮናስም እግዚአብሔር የሰማይ እና የምድር የቀላያት እና የአብርሕት ፈጣሪ መሆኑን እያወቀ እያስተማረ ከእርሱ ዓይን እይታ ለመራቅ እግዚአብሔር በፈጠረው ባሕር ላይ በመርከብ ተሳፍሮ ሊሸሽ መሞከሩ በራሱ የዋህ ያስብለዋል። በተጨማሪም አብረውት የነበሩ ነጋድያን ከየት ወገን እና ከየት እንደመጣ ሲጠይቁት የሚመልሰው መልስ በራሱ የዋህነቱን ያሳያል የመጀመርያውዕብራዊ ነኝሲል መልሷል ዕብራዊ መሆን ሃይማኖት አዋቂ እና ሃይማኖተኛ መሆንን ያሳያል። ሁለተኛው ደግሞባሕሩን እና የብሱን የፈጠረን አመልካለሁብሎ ባህር ፈጣሪ ዐይን እይታ ለመራቅ ወደ ተርሴስ ለመሄድ መሞከሩ በእርግጥም የዋህ የሚያሰኘው ነው።
ሌላው ደግሞ ዮናስን ያስጨንቀው የነበረው የራሱ ቃል (ትንቢት) ተፈጻሚነት አለማግኘቱ እንጂ የነነዌ ሰዎች በእነርሱ ላይ ሊደርስ ከነበረው መዓት መዳን አለመዳናቸው አልነበረም። የሚያስደንቀው ደግሞ በእግዚአብሔር ቸርነት የእርሱ ቃል (ትንቢት) ተፈጻሚነት እንደ ማይኖረው አውቆ ወደ ተላከበት ላለመሄድ አጥብቆ መጠየቁ ነው። ዮና 42
የእግዚአብሔር ነቢይ ለራሱ ቃል ተጨንቆ እንዲህ ያለ የተማጽኖ ቃል ቢያሰማ በእርግጥም ከየዋህነት እንጂ ሳያውቅ ቀርቶ አደለም።አቤቱ እለምንሃለሁ በሀገሬ ሳለሁ የተናገርኩት ይህ አልነበረም? አንተ ይቅር ባይ ታጋሽ ምሕረትህም የበዛ ከክፉው ነገር የምተጸጸት አምላክ እንደሆንክ አውቄ ነበርና᎐᎐᎐ብሎ የእግዚአብሔር ቸርነት ማድረግ አሳዝኖት፣ የርሱ ታማኝነት የሚያሳጣ መስሎት አዘነ።
ዮናስ ያዘነው ሰብአ ነነዌ በመዳናቸው ሳይሆን የእርሱ ቃል በእግዚአብሔር መሸፈኑ ነው። ነገር ግን ይህ በራሱ የዮናስን የዋህነት ያሳያል ይኸውም ሰብዓ ነነዌ ገና የርሱን ቃል ሰምተው እንደዚያ ያለ ለውጥ ማምጣታቸው በራሱ የእርሱን ታማኝነት ያሳያል። ምክያቱም ገና አንድ ዐረፍተ ነገር ተናግሮ እንዲያ ለመዳን መንቀሳቀሳቸው የቱን ያህል ቃሉን እነዳመኑትና እንደተቀበሉት ያሳያል! ይህንንም አለማስተዋሉ የዋህነቱን ይመሰክራል።
እግዚአብሔርም የዋህነቱን ስለሚያውቅ ሲያባብለው እና በተለያየ ሁኔታ እና ምሳሌ ሲያስተመረው እናያለን።በውኑ ትቆጣ ዘንድ ይገባሃልንእያለ ይናገረው ነበር ዮና 49 እሰከ መጨረሻ። በእውነት በፍጹም ክፋት አስቦት ቢሆን ኖሮ ሲጀመር እግዚአብሔርም እንዲያስተምርለት አያዘውም ነበር። “᎐᎐᎐ በዓይኑ ትዕቢተኛ የሆነውን እና ልቡ የሚሳሳው ከእኔ ጋር አይተባበርምእንዲል መዝ 100 5
ሌላው የነነዌ ሰዎች በንስሓ ሕይወት በመለወጥ እንደምሳሌ የሚጠቀሱ ናቸው። ይኸውም ገና በከተማዋ ገብቶበሦስት ቀን ወስጥ ትገለበጣለችስላለ ብቻ ሀገሩም አመነው አዋጅን አውጀው ፍጹም ጾምን ጾሙ፤ የእግዚአብሔርን መዓት በምሕረት መልሰዋል። የነነዌ ሰዎች ነቢዩ ዮናስ ገናትገለበጣለችስላለ ብቻ ሀገሬው ሙሉ ከንጉሥ እስከ ገረድ ከልኂቅ እስከ ደቂቅ ሆነው ለለውጥ መነሳታቸው በራሱ ሙሉ በሙሉ የንስሓ ሕይወታቸውን የሚያረጋግጥ ነው።
በአሁኑ ጊዜ መምህራን ሁሉ ትምህርተ ሃይማኖትን እያስተማሩ የንስሓ ሕይወትን እየሰበኩ ለውጡ ግን የትምህርቱን ያህል አለመሆኑ የሰሚውን ጉድለትና ደካማነት ያሳያል “᎐᎐᎐ዳሩ ግን የሰሙት ቃል ከሰሚዎቹ ጋር በእምነት ስላልተዋሓደ አልጠቀማቸውምዕብ 42 እንዲል። ልብ እንበል! ነቢዩ ዮናስ ለሰብአ ነነዌ የተናገረውበሦስት ቀን ውስጥ ነነዌ ትገለበጣለችየሚል አምስት ቃልን ብቻ ነው በዚህች ቃል ብቻ ይህን የመሰለ ለውጥ ማምጣት መቻል በራሱ ፍጹም የእግዚአብሔርን ሥራ እንድናደንቅ ይረዳናል።
ስለ ነነዌ ሰዎች የንስሓ ሕይወት ጌታ ራሱ በወንጌሉ መስክሯል። ለሕዝቡም መፈራረጃ አድርጓቸዋል። ሉቃ 1932 “᎐᎐᎐በዮናስ ስብከት ንስሓ ገብተዋልናእንዲል። በተጨማሪም የነነዌ ሰዎች በፍርድ ቀን ከዚህ ትውልድ ጋር ይፈርዱበታ ይላል ማቴ 1241
ሌላው እግዚአብሔር መቼም ቢሆን ሰው የተመኘውን አያስቀርም። አዳም አምላክነትን ተመኘ ዘመኑ ሲፈጸም አምላክ ሰው ሆኖ ተምኔቱን (ምኞቱን) ፈጽሞለታል። ዮናስም ምንም እንኳን በቀጥታ እንዲጠፉ ባይፈልግም ውሸታም እንዳይባል ስለሚፈልግ ቀድሞ በተናገረው ቃል መሠረት ትንቢቱ ተፈጽሟል። ዮናስ በሦስት ቀን ውስጥ እንዳለ በሦስተኛው ትውልድ ተወግታ ጠፍታለች።
የመጨረሻው ዮናስ ለክርስቶስ ምሳሌው ሆኗል። ይኽውም በሉቃ 1130 “ ዮናስ ለነነዌ ሰዎች ምልክት እንደሆናቸው እንዲሁ ደግሞ የሰው ልጅ ለዚህ ትውልድ ምልክት ይሆናልእንዲል። በጌታ ሞትም ምሳሌውሆኗልክፉና አመንዝራ ትውልድ ምልክትን ይሻል ከነቢዩ ከዮናስ ምልክት በቀር ምልክት አይሰጠውም ዮናስ በዓሣ አንበሪ ሆድ ሦስት ቀን እና ሦስት ሌሊት እንደ ነበር እንዲሁ ሰው ልጅ በምድር ልብ ውስጥ ሦስት ቀን እና ሦስት ሌሊት ይኖራልእንዲል ማቴ 1239
ሰለዚህ እንዲህ ያሉትን ነገር እያሰቡ የነነዌን ሀገር ሰዎች ተግባር ማየት ከእነርሱም መማር ያስፈልጋል እግዚአብሔር ዕድሜ ለንስሐ ዘመን ለፍሥሃ ያድለን
ለንስሐ ሞት ያብቃን!!

No comments:

Post a Comment