ጥቅስ

ጌታዬ
እግዚአብሔር ሆይ
እስከዚህ ያደረስኸኝ
እኔ ማን ነኝ ?
ቤቴስ ምንድር ነው?
2 ሳሙ 7፥18

Wednesday, 12 December 2012

በዓታ ለማርያም

                                    ዲያቆን መልአኩ እዘዘው
እመቤታችን በ5485 ዓ.ዓ ከአባቷ ከኢያቄም ከእናቷ ከሐና እም ሊባኖስ ትወጽዕ መርዓት፡፡ ከሊባኖስ ሙሽራ ትወጣለች” ተብሎ በተነገረው መሠረት ነሐሴ 7 ቀን ተጸነሰች፡፡ግንቦት አንድ ቀን ሊባኖስ በምትባል ወረዳ በብጽአት እንደተወለደች የቤተክርስቲያን ታሪክ በሰፊው ያስረዳል፡፡ በጾም በጸሎት በአስተብቁዖት የተገኘች ናት፡፡ ንጽሕት በመሆኗም ማኅደረ እግዚአብሔር ሆናለች፡፡
ከዚህ በኋላ እመቤታችን መዋዕለ ጥብ እስክታደርስ ድረስ በአባት እናቷ ቤት 3 ዓመት ተቀመጠች፡፡ ከመዝ ነበረት ውስተ ቤተ አቡሃ ወእማ 3ተ ዓመተ እንዘ ትጠቡ ሐሊበ እማ (እንዳለ በነገረ ማርያም፡፡)

ኢያቄምና ሐናም ልጃቸውን ሲያሰሳድጉና ስላደረገላቸውም ሁሉ እግዚአብሔርን ፈጽመው ሲያመሰግኑት ሦስት ዓመት ኖሩ። በጾም፤ በጸሎት ተወስነው ለድሆችና ለጦም አደሮች ምፅዋት እየሰጡ በጐ ሥራ መሥራትን አበዙ።

ልጃቸውንም ድንግል ማርያምን በንጽሕና ሲያሳድጉ ሦስት ዓመት በተፈጸመ ጊዜ ሐና ባሏን ኢያቄምንወንድሜ ሆይ ልጃችንን ለቤተ እግዚአብሔር ብፅዐት አድርገን እንስጥ። ልጃችን ቤተ እግዚአብሔርን ልታገለግል እንጂ በዚህ ዓለም እኛን ልታገለግል እንዳልተሳልን አስብ አለችው።ኢያቄምም ይህን ነገር ከሚስቱ በሰማ ጊዜ ደስ አለው።


ነብየ እግዚአብሔር ዳዊት ልጄ ሆይ ስሚ እዪ ጆሮሸንም አዘንብዪ ወገንሽን የአባትሽንም ቤት እርሺ ንጉሥ/ክርስቶስ/ ውበትሽን /ንጽሐ ባሕርይሽን/ ወድዶአልና መዝ 44÷10-11 ብሎ እንደተናገረ ለወላጆቿ የብፅዐት ልጅ የሆነችው ድንግል ማርያም ሆዷ ዘመድ ሳይወድ አፏ እህል ሳይለምድ ከእናቷና ከአባቷ ተለይታ ታህሣሥ ሦስት ቀን በሦስት ዓመት ወደ መቅደሰ ኦሪት ገብታለች። በአታ ለማርያም ማለትም የድንግል ማርያም ወደ ቤተ መቅደስ መግባት ማለት ነው።

ከዚህም በኋላ በ3 ዓመት ልተተ ሕፃናትን ፈጸመች አበ እመ እያለች ታጫውት ጀመር እነርሱም ከእንግዲህ ወዲህማ ስእለት መብለት ይሆንብን የለምን ወስደን እንስጥ ብለው ይዘዋት ወደ ቤተ መቅደስ ሲሄዱ ዘካርያስም ሕዝቡን ሰብስቦ ጉባዔ አድርጎ ሲያስተምር ቆያቸው ከዚያውም ደርሰው እነሆ ተቀበሉን አሏቸው እነርሱም እንቀበላለን ብለው ቢያዩዋት ከፀሐይ 7 እጅ አብርታ ዕንቈ ባሕርይ መስላ ታያቻቸው እነርሱም እኛ ይህችን የመሰለች ፍጡር ምን እናደርጋታለን ምን እናበላታለን ምን እንጋርድላታለን ብለው ሲጨነቁ ከዚህም መካከል እመቤታችንን እግዝእትነ ማርያም መንፈሳዊ ረኅብ ተነስቶባት ምርር ብላ አለቀሰች፡፡

ያን ጊዜ መልአኩ ፋኑኤል በመሶበ ወርቅ ኅብስት ሰማያዊ ፤ በብርሃን ጽዋ ስቴ ሕይወት ይዞ ረቦ ታያቸው ሕዝቡም ዘካርያስን አባታችን ይህ የወረደው ክብር ላንተ እንደሆነ ተነስተህ ታጥቀህ እጅ ነስተህ ሰግደህ ተቀበል አሉት፡፡ ዘካርያስም እሽ ብሎ እጅ ነስቶ ሰግዶ እቀበላለሁ ብሎ ሲያይ ወደሰማይ እራቀው መጠቀው፡፡ ከሕዝቡም እያንዳንዱ እየተነሱ እንቀበላለን ብለው ቢያዩ ወደሰማይ ራቃቸው መጠቃቸው፡፡

ከዚህም በኋላ ዘካርያስ ሐናን ጠርቶ ለናንተ ለእንግዶች የወረደ ክብር እንደሆነ ሕፃኒቱን ይዘሽ ወደዚያ ፈቅ ብለሽ ተቀመጪ አላት፡፡ እርሷም ሕፃኒቱን ይዛ ወደዚያ ፈቅ ብላ ተቀመጠች፡፡ መልአኩም ከራሳቸው ላይ ረቦ አልወርድም አለ፡፡

Monday, 10 December 2012

ኤልያስ

ኤልያስ
እነሆ የተባረከ የታህሳስ ወር ባተ፤ ይህ ወር ቀኑ 9 ሰዓት ነው ሌሊቱ 15 ሰዓት፤ ቀኑ በጣም አጭር ነው ፤ ቶሎ ይመሻል ሌሊቱ በጣም ረጅም ነው፤ ታህሳስ 1 በዚህች ቀን በገለዓድ ይኖር የነበረው ቴስብያዊው ኤልያስ የተወለደበት ቀን ነው፤ ታሪኩ 1ኛ ነገስት 17፤1 ላይ በስፋት ይገኛል፤ በእሳት ሰረገላ የተሰወረው ጥር 6 ቀን ነው፤ እነዚህን ሁለት ቀናት ቤተክርስቲያን ነብዩን አስባ ትውላለች፤ ይህ ነብይ በአገራችን በስሙ የታነጹለት አብያተክርስቲያናት አሉት:: ከነዚህም በመዲናችን አዲስ አበባ እንጦጦ ጋራ ላይ የሚገኘው ቤተክርስቲያን አንዱ ነው፤ ኤርትራ ውስጥም አንድ ቤተክርስቲያን አለው፤ ዛሬ በደማቁ ተከብሮ ይውላል፡፡ አክአብና ኤልዛቤል ምሰኪኑን ናቡቴ ከአባቶቹ እርስት አፈናቅለው በግፍ በገደሉት ጊዜ፤ ንጉሱን ሳይፈራና ሳያፍር በግልጽ የዘለፈ ነብይ ነው፤ ዝናብ እንዳይዘንብ ሰማይንም የለጎመ ነው ይህንንም ያዕቆብ በመልእክቱ እንዲህ ሲል መስክሯል ያዕ 5 ፤ 16 "የጻድቅ ሰው ጸሎት በሥራዋ እጅግ ኃይል ታደርጋለች። ኤልያስ እንደ እኛ የሆነ ሰው ነበረ፥ ዝናብም እንዳይዘንብ አጥብቆ ጸለየ፥ በምድርም ላይ ሦስት ዓመት ከስድስት ወር አልዘነበም፤ ሁለተኛም ጸለየ፥ ሰማዩም ዝናብን ሰጠ ምድሪቱም ፍሬዋን አበቀለች"

ከበዓሉ በረከት ያሳትፈን፡፡

Saturday, 8 December 2012

ተፍጻሚ ሰማዕት ቅዱስ ጴጥሮስ

ተፍጻሚ ሰማዕት ቅዱስ ጴጥሮስ ህዳር 29 አረፈ::
ተፍጻሜ ሰማዕት ጴጥሮስ ሦስት ደቀ መዛሙርት ነበሩት አርዮስ፤አኪላስና እለእስክንድሮስ ይባላሉ::
ለአርዮስ ክህነት ሰጥቶ የሾመው ተፍጻሜ ሰማዕት ጴጥሮስ ነው:: አርዮስ ግን አጥብቆ ተመራመረ ወልድ ፍጡር ነው ብሎ ወደቀ::
አርዮስ ወልድ ፍጡር ነው ብሎ በድብቅ ለሰው ማስተማር ጀመረ:: በዚህ ጊዜ ጌታችን ለተፍጻሚተ ሰማዕት ጴጥሮስ የተቀደደ ልብስ ለብሶ ተገለጸለት
ተፍጻሚ ሰማዕት ቅዱስ ጴጥሮስ :- አንተ ማን ነህ?
...
ኢየሱስ :- የናዝሪቱ ኢየሱስ ነኝ
ተፍጻሚ ሰማዕት ቅዱስ ጴጥሮስ :- ታዲያ ልብስህ ለምን ተቀደደ ?
ኢየሱስ :- “አርዮስ ሰጠጣ ለልብስየ” አርዮስ ልብሴን ቀደደው :: ከባህሪ አባቴ ከአብ ከባህሪ ህይወቴ ከመንፈስ ቅዱስ ለይቶ ፍጡር ነው አለኝ ::
ተፍጻሚ ሰማዕት ቅዱስ ጴጥሮስ ይህን ራዕይ እይቶ ብዙም ሳይቆይ አርዮስ መጣ ቁጭ አድርጎ መከረው “በልብህ ያለውን ኑፋቄ ካሰብክ እንዳትናገር ከተናገርክ እንዳትደግመው ብሎም ያስጠነቅቀዋል፤ ሊሰማው ግን አልቻለም፤ አውግዞ ይለየዋል:

Tuesday, 4 December 2012

ቅዱስ መርቆሪዎስ ሰማዕት

+ህዳር 25 ቀን ቅዱስ መርቆሪዎስ በሰማዕትነት አረፈ፤ አገሩ ሮም ነው፤ በወጣትነቱ ከሃዲው ንጉስ ኡልያኖስ ላቆመው ጣኦት አልሰግድም ብሎ የሰው ልጅ ሊሸከመው የማይችለውን መከራ ተቀበለ፤በመጨረሻም ህዳር 25 ቀን አንገቱን ቆርጠው ገደሉት ደም ውኃና ወተት ከአንገቱ ፈሰሰ። ይህ ሰማዕት በአገራችን በስሙ በርካታ ገዳማትና አብያተክርስቲያናት አሉት በተለይም ቅዱስ ላሊበላ ካነጻቸው 11 ውቅር አብያተክርስቲያናት አንዱን ቤተ መርቆሪዎስ ብሎ ሰይሞለታል፤ በዚህ በሰሜን ሸዋ ደግሞ የሚገርም ገዳም አለው፤ ካህናት በማህሌት ወረብ ሲያቀርቡ ስዕሉ ያሸበሽባል ይዘላል፤ ይህንንም አይቶ ማረጋገጥ ይቻላል፤ በመዲናችን አዲስ አበባ ቅዱስ ኡራኤል ቤተክርስቲያን ውስጥ ታቦቱ አለ:: ዛሬ በደማቁ ተከብሮ ይውላል። መርቆሪዎስ ከሞተ በኃላ ፈረሱ ለሰባት ዓመት ወንጌልን አስተምሯል፤ በኃላም አንገቱን ቆርጠው ገድለውታል እንዴት ብሎ የሚገረም የበልአምን አህያ ይጠይቃት፤ እኛስ እስመ አልቦ ነገር ዘይሳኣኖ ለእግዚያብሔር ብለን እንመልሳለን፤ ዘኁልቁ 22፤28 ቅዱስ ጴጥሮስም እንዲህ አለ ቃል የሌለው አህያ በሰው ቃል ተናግሮ የነብዩን እብድነት አገደ ይላል 2ጴጥ 2፤16። ከ ከሰማዕቱ ቅዱስ መርቆሪዎስ  አመታዊ በዓል  በረከት ያሳትፈን አሜን !!!

Tuesday, 27 November 2012

አባ ገሪማ ዘመደራ

                                                                               †አባ ገሪማ ዘመደራ†


አባ ገሪማ ዘመደራ (“ኦ ወልድዬ ግሩም ገሪማ ገረምከኒ”)

የተሰዓቱ ቅዱሳን ሐዋርያዊ ተልእኮ መቅድም
ተሰዓቱ ቅዱሳን ወደ ኢትዮጵያ የመጡት አልአሜዳ በነገሰ በአምስት ዓመት ነው። እንደመጡት እንደ አንድ ልብ መካሪ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ ሆነው በአክሱም ዐስራ ሁለት ዓመት ኖረዋል።
ተሰዓቱ ቅዱሳን በስም አባ አሌፍ፣ አባ አረጋዊ፣ አባ
 
 ጰንጠሌዎን፣ አባ ገሪማ፣ አባ ጵሕማ፣ አባ አፍአባ ሊቃኖስ፣ አባ ይምዓታ አባ ጉባ ይባላሉ። እኚ አባቶች ወደ ኢትዮጵያ እንደገቡ ዝም ብሎ አልተቀመጡም፤ ለሥራቸው በር ከፋች የሆነውን ቋንቋ፣ የሕዝቡን ባህል ጠንቅቀው ካወቁ በኋላ ላይ በአንድ አከባቢ ከመኖር ይልቅ መንፈስ ቅዱስ በመደባቸው ቀጥታ ማስተማርን መርጠው መንፈሳዊ ዓላማቸውን ለማሳካት የአክሱምን ነገስታት እርዳታና ድጋፍ አልተለያቸውም ነበር። እኚው ተሰዓቱ ቅዱሳን የመጡበት ሀገራት ሮም፣ እስያ፣ አንጾኪያ፣ ቁስጥንጥንያ፣ ቂሳርያ፣ ኪልቂያ ሲሆን በነበሩበት ጊዜያትም፡­-
፩. ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን አጽንቶልናል።
፪. መጽሐፍትን ተርጉሞልናል።
፫. ስብከተ ወንጌልን አስፋፍተዋል።
፬. ብዙ ገዳማትን መስርተዋል።
፭. ሥርዓተ ምንኩስናን አደራጅተዋል።
ስለ እነዚህ ቅዱሳን ይህችን ታህል ካልኩኝ ዛሬ ወርሃዊ ዕለታቸው ከሚታሰበው ከእነዚሁ ቅዱሳን አንዱ ስለሆኑ አባ ገሪማ ዘመደራ ትንሽ ልበላችሁ።
አባ ገሪማ ዘመደራ፡­- ቀዳሚ ስማቸው ይስሐቅ ነው። አባታቸው ሶፎንያስ ንጉስ ሮም ነው። አባ ገሪማ ከልጅነታቸው ጀምሮ በመንፈሳዊ ትምህርት ታንጸው አድገው ቤተ ክርስቲያንን ሲያገለግሉ ኖረዋል። ኋላም የአባታቸውን ዙፋን ወርሰው ለ፯ ዓመት ገዝተዋል። ከዚህ በኋላ አባ ጰንጠሌዎን “ምድራዊ መንግስት ያልፋል ይጠፋል፤ የማያልፈውን ሰማያዊ መንግስት ትወርስ ዘንድ ፈጥነህ ወደኔ ና።” ብለው ላኩባቸው። ቅዱስ ገብርኤል ከእግዘዚአብሐሔር ታዞ በክንፉ ነጥቆ በአንድ ቀን አክሱም አድርሷቸው ተገኙ። መዓርገ ምንኩስናን ተቀብለው ሥጋቸው አልቆ አጥንታቸው

እንኳን ለኅዳር ጽዮን በሰላም አደረሳችሁ

          እምነ ጽዮን - እናታችን ጽዮን                   

እንኳን ለኅዳር ጽዮን በሰላም አደረሳችሁ
በቅዱሳት መጻሕፍት ጽዮን የሚለው ቃል ተደጋግሞ በነቢያቱ ተነግሯል፡፡ ሆኖም የጽዮን ትርጉም እንደተነገረበት ዐውደ ትንቢት እንደተሰበከበት መዋዕለ ትምህርት ምስጢሩ ይለያያል፡፡
ድንግል ማርያም ምስለ ፍቁር ወልዳ
ታቦተ ጽዮን በፈቃደ እግዚአብሔር በነቢዩ ሙሴ አማካኝነት ለሰው ልጆች ተሰጥታ እስራኤላውያን ሲባረኩባት፣ መሥዋዕታቸውን ሲያቀርቡባት ከእግዚአብሔር ሲታረቁባት ኖረዋል፡፡ከአራት ሺሕ ሦስት መቶ ሃያ ሰባት ዓመተ ዓለም (4327 ዓ.ዓ.) ጀምሮ ለአርባ ዓመታት ያህል እስራኤላውያንን በክህነት ያገለግል የነበረው ካህኑ ዔሊ ዕድሜው ሲገፋ ሁለት ልጆቹን ጠርቶ ምሉዕና ዱግ /ዋናና ምክትል/ አድርጎ ሾማቸው፡፡

Friday, 23 November 2012

ሰማዕቱ ቅዱስ ሚናስ

                                           ሰማዕቱ ቅዱስ ሚናስ


ከቅዱሳን
ሰማዕታት አንዱ የሆነው ማር ሚና 4ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ተጋድሎውን የፈፀመ ግብፃዊ ሰማዕት ሲሆን ህዳር 15 ቀን የሚነበበው ስንክሳር ቅዱስ ሚናስ በሚል ስያሜ ይገልፀዋል። በሶሪያ ቋንቋ ማር የሚለው ቃልቅዱስየሚልትርጉም ሲኖረው ለወንድ የሚሰጥ ቅጥያ ሲሆን ለሴት ደግሞ ማርታ ይሆናል ይሄውም ቅድስት ማለት ነው።
ቅዱስ ሚናስ ከእናቱ ከአውፌምያ እና ከአባቱ ከአውዶስዮስ ልዩ ስሙ ኒቆስ ሻቲ በተባለ መንደር 276 ተወለደ። እናቱ አውፌምያ ልጅ መውለድ ባለመቻሏ ታዝንና ትጨነቅ ነበር። ወደ ቤተ-ክርስቲያን ስትሄድም እናቶች ልጆቻቸውን ሲያቆርቡ ስታይ በማልቀስ ፈጣሪዋን ልጅ እንዲሰጣት ትለምን ነበር። እግዚአብሔርም የልመናዋን ቃል ሰምቶ ወንድ ልጅ ሰጣት።