ጥቅስ

ጌታዬ
እግዚአብሔር ሆይ
እስከዚህ ያደረስኸኝ
እኔ ማን ነኝ ?
ቤቴስ ምንድር ነው?
2 ሳሙ 7፥18

Saturday 8 December 2012

ተፍጻሚ ሰማዕት ቅዱስ ጴጥሮስ

ተፍጻሚ ሰማዕት ቅዱስ ጴጥሮስ ህዳር 29 አረፈ::
ተፍጻሜ ሰማዕት ጴጥሮስ ሦስት ደቀ መዛሙርት ነበሩት አርዮስ፤አኪላስና እለእስክንድሮስ ይባላሉ::
ለአርዮስ ክህነት ሰጥቶ የሾመው ተፍጻሜ ሰማዕት ጴጥሮስ ነው:: አርዮስ ግን አጥብቆ ተመራመረ ወልድ ፍጡር ነው ብሎ ወደቀ::
አርዮስ ወልድ ፍጡር ነው ብሎ በድብቅ ለሰው ማስተማር ጀመረ:: በዚህ ጊዜ ጌታችን ለተፍጻሚተ ሰማዕት ጴጥሮስ የተቀደደ ልብስ ለብሶ ተገለጸለት
ተፍጻሚ ሰማዕት ቅዱስ ጴጥሮስ :- አንተ ማን ነህ?
...
ኢየሱስ :- የናዝሪቱ ኢየሱስ ነኝ
ተፍጻሚ ሰማዕት ቅዱስ ጴጥሮስ :- ታዲያ ልብስህ ለምን ተቀደደ ?
ኢየሱስ :- “አርዮስ ሰጠጣ ለልብስየ” አርዮስ ልብሴን ቀደደው :: ከባህሪ አባቴ ከአብ ከባህሪ ህይወቴ ከመንፈስ ቅዱስ ለይቶ ፍጡር ነው አለኝ ::
ተፍጻሚ ሰማዕት ቅዱስ ጴጥሮስ ይህን ራዕይ እይቶ ብዙም ሳይቆይ አርዮስ መጣ ቁጭ አድርጎ መከረው “በልብህ ያለውን ኑፋቄ ካሰብክ እንዳትናገር ከተናገርክ እንዳትደግመው ብሎም ያስጠነቅቀዋል፤ ሊሰማው ግን አልቻለም፤ አውግዞ ይለየዋል::
ጓደኞች አኪላስና እለእስክንድሮስ ሊማልዱለት ይመጣሉ፤ አባታችን አርዮስ ተመልሻለው እያለ ነው ከግዝቱ ፍታው ይሉታል፤ እርሱም እንደማይመለስ ጌታ በራዕይ ነግሮኛል አሁን እኔ የምሞትበት ጊዜ ደርሷል ከኔ በኃላ አኪላዎስ ሊቀ ጳጳስ ትሆናለህ ጓደኝነት በልጦብህ አርዮስን ከግዝቱ ትፈታዋለህ ነገር ግን ብዙ አትቆይም ትሞታለህ ብሎ ትንቢት ይነግራቸዋል::
የእረፍቱ ቀን እንደደረሰም አውቆ “ጌታ ሆይ የኔን ሞት የሰማእታት መጨረሻ አድርግሊኝ ከኔ በኋላ የአንድስ እንኳን ሰማእት ደም አይፍሰስ” ብሎ ጸለየ:: ህዳር 29 ቀን የዲዮቅልጥያኖስ ጭፍሮች አንገቱን ቆርጠው ገድለውታል:: ለዚህም “ተፍጻሚ ሰማዕት ጴጥሮስ” ብላ ቤተክርሰቲያን የምትጠራው የሰማእታት መጨረሻ ማለት ነው::

++የተፍጻሚ ሰማዕት ቅዱስ ጴጥሮስ ረድኤት በረከቱ ምልጃና ጸሎቱ ከሁላችን ጋር ለዘላለሙ ጸንቶ ይኑር +++

No comments:

Post a Comment