ጥቅስ

ጌታዬ
እግዚአብሔር ሆይ
እስከዚህ ያደረስኸኝ
እኔ ማን ነኝ ?
ቤቴስ ምንድር ነው?
2 ሳሙ 7፥18

Tuesday 4 December 2012

ቅዱስ መርቆሪዎስ ሰማዕት

+ህዳር 25 ቀን ቅዱስ መርቆሪዎስ በሰማዕትነት አረፈ፤ አገሩ ሮም ነው፤ በወጣትነቱ ከሃዲው ንጉስ ኡልያኖስ ላቆመው ጣኦት አልሰግድም ብሎ የሰው ልጅ ሊሸከመው የማይችለውን መከራ ተቀበለ፤በመጨረሻም ህዳር 25 ቀን አንገቱን ቆርጠው ገደሉት ደም ውኃና ወተት ከአንገቱ ፈሰሰ። ይህ ሰማዕት በአገራችን በስሙ በርካታ ገዳማትና አብያተክርስቲያናት አሉት በተለይም ቅዱስ ላሊበላ ካነጻቸው 11 ውቅር አብያተክርስቲያናት አንዱን ቤተ መርቆሪዎስ ብሎ ሰይሞለታል፤ በዚህ በሰሜን ሸዋ ደግሞ የሚገርም ገዳም አለው፤ ካህናት በማህሌት ወረብ ሲያቀርቡ ስዕሉ ያሸበሽባል ይዘላል፤ ይህንንም አይቶ ማረጋገጥ ይቻላል፤ በመዲናችን አዲስ አበባ ቅዱስ ኡራኤል ቤተክርስቲያን ውስጥ ታቦቱ አለ:: ዛሬ በደማቁ ተከብሮ ይውላል። መርቆሪዎስ ከሞተ በኃላ ፈረሱ ለሰባት ዓመት ወንጌልን አስተምሯል፤ በኃላም አንገቱን ቆርጠው ገድለውታል እንዴት ብሎ የሚገረም የበልአምን አህያ ይጠይቃት፤ እኛስ እስመ አልቦ ነገር ዘይሳኣኖ ለእግዚያብሔር ብለን እንመልሳለን፤ ዘኁልቁ 22፤28 ቅዱስ ጴጥሮስም እንዲህ አለ ቃል የሌለው አህያ በሰው ቃል ተናግሮ የነብዩን እብድነት አገደ ይላል 2ጴጥ 2፤16። ከ ከሰማዕቱ ቅዱስ መርቆሪዎስ  አመታዊ በዓል  በረከት ያሳትፈን አሜን !!!

1 comment:

  1. የሰማዕቱ የቅዱስ መርቆሪዎስ ቤተክርስቲያን በምንጃር በሸንኮራም ይገኛ....በህዳር እና በጥር 25 ቀን ይነግሳል::አሜን ከሰማዕቱ ቅዱስ መርቆሪዎስ በረከት ያሳትፈን

    ReplyDelete