ክፍል አንድ (1) ሳሚ ዘቂርቆስ
በዚህ ክፍል አንድ ትምህርታችን ምሥጢረ ተክሊል ምንድን ነው? የሚለውን ከብዙ በጥቂቱ እንመለከታለን፡፡1. ምሥጢረ ተክሊል ምንድን ነው?
ቤተክርስቲያን የክርስቲያን ቤት ናት ፤ጥበብ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፤በሰባቱ ምሶሶዎቿ ቤቷን አንጻለች፡፡ እነዚህ ምሶሶዎች ደግሞ የምድር ሥርዓት እስከ ሚጠናቀቅበት ድረስ የማይናዱ፤የማይፈርሱ፤የማይለወጡ፤የማይሻሩ እና አላፊ ያልሆኑ ዘላለማዊ እና ሰማያዊ ጸጋዎችን የሚያሰጡ በሚታይ ነገር ፤ የማይታይን ሀብት ለሁላችን እንድንካፈል የሚያደርጉ ቤተክርስቲያንን በምሶሶነት የሚደግፉ ምሥጢራት ቤተክርስቲያን ናቸው፡፡ ጠቢቡ ሰሎሞን እንዲህ ሲል እግዚአብሔር ስላዘጋጀልን ምሥጢራት ይገልጣል፡-" ጥበብ ቤትዋን ሠራች፤ሰባቱንም ምሶሶችዋን አቆመች፡፡ ፍሪዳዋን አረደች፤የወይን ጠጅዋን ደባለቀች፡፡" ምሳ9፡1
ወዳጆቼ ሁላችን እንደምናውቀው በምሶሶ የተመሰሉት ሰባቱ ምሥጢራተ ቤተክርስቲያን፡- 1. ምሥጢረ ጥምቀት 2. ምሥጢረ ቁርባን 3. ምሥጢረ ሜሮን 4. ምሥጢረ ንስሐ 5. ምሥጢረ ክህነት 6. ምሥጢረ ተክሊል 7. ምሥጢረ ቀንዲል ናቸው፡፡





