ምንኵስናና ተጋድሎ
ዐፄ ዳዊት የአባ ጊዮርጊስን ሊቅነትና መልካም ሥነ ምግባር በሚገባ ስላወቀ በጋብቻ ሊዛመደው ወዶ ስለ ነበር ልጁን እንዲያገባ ዘወትር ይጠይቀው ነበር፡፡ አባ ጊዮርጊስ ግን በድንግልና ጸንቶ ለመኖር እንደ ሚገልግ ከመግለጽ አልተቆጠበም ነበር፡፡ የዐፄ ዳዊት ጥያቄ ስለበዛበት ከአካባቢው በመሸሽ ከአባ በጸሎተ ሚካኤል መቃብር ደረሰ፡፡ አባ በጸሎተ ሚካኤልን ከልጅነቱ ጀምሮ ይወዳቸው ስለነበር እርሳቸው በመሠረቱት ገዳም በመልካም ሥነ ምግባራቸው ከታወቁት የአባ ቴዎድሮስ ዘንድ የምንኵስና ልብስ ለብሶ መነኮሰ፡፡
ከመነኮሰ በኋላ ወደ ሸግላ በመምጣት ‹‹ወእምድኀረዝ ኮነ አቡነ ጊዮርጊስ መምህር ለነገሥት ወለካህናት ዘደብተራ ወለኩሉ ዐበይተ ቤተ መንግሥት፣ ለንቡራነእድ ወለመኳንንት፣ ለመሳፍነት ወለኩሉ ተዐይነ ቤተ መንግሥት ከዚህ በኋላ ለነገሥታትና በቤተ መንግሥቱ ለነበሩ ካህናት እንዲሁም በቤተ መንግሥቱ ታላላቆች ለነበሩ፣ ለንቡራነእድ ለመኳንንት፣ ለመሳፍንትና በቤተ መንግሥቱ ለነበሩ ባለሟሎች ሁሉ መምህር ሆነ፡፡››
አባ ጊዮርጊስ በሸግላ በነበረ ጊዜ በወባ በሽታ ታምሞ ሊሞት ደርሶ እንደ ነበር ገድሉ ይናገራል፡፡ታምሞ በነበረ ጊዜ አንድ ሌሊት ቅዱስ ጴጥሮስና ቅዱስ ጳውሎስ ተገልጠውለት ከእኛ ጋር ትኖር ዘንድ ልንወስድህ መጣን አሉት፡፡ እርሱም የድርሰት ሥራዬን ሳልሠራና እግዚአብሔርንም አብዝቼ ሳላመሰግነው አሁን አትውሰዱኝ ሲል ለመነ፡፡ እነርሱም ልመናውን ተቀብለውት ከሕመሙ ፈውሰውት ሔዱ፡፡ ለዚህም ይመስላል ከበሽታው እንደ ተፈወሰ ወዲያው የድርሰት ሥራውን የጀመረው፡፡
የመጀመሪያ መጽሐፉን ጽፎ እንደ ጨረሰ ጠፍቶበት እንደ ነበር ገድሉ ይተርካል፡፡ በቤቱ ውስጥ የነበሩትን መጻሕፍት ሁሉ እያገላበጠ ቢፈልገውም ሊያገኘው አልቻለም፡፡ አንድ ቀን በቤተክርስቲያን ሌሊት በአገልግሎት ላይ እያለ እመቤታችን ተገልጣ






