ዲያቆን መልአኩ እዘዘው
እመቤታችን በ5485 ዓ.ዓ ከአባቷ ከኢያቄም ከእናቷ ከሐና “እም ሊባኖስ ትወጽዕ መርዓት፡፡ ከሊባኖስ ሙሽራ ትወጣለች” ተብሎ በተነገረው መሠረት ነሐሴ 7 ቀን ተጸነሰች፡፡ግንቦት አንድ ቀን ሊባኖስ በምትባል ወረዳ በብጽአት እንደተወለደች የቤተክርስቲያን ታሪክ
በሰፊው ያስረዳል፡፡ በጾም በጸሎት በአስተብቁዖት የተገኘች ናት፡፡ ንጽሕት በመሆኗም
ማኅደረ እግዚአብሔር ሆናለች፡፡
ከዚህ በኋላ እመቤታችን
መዋዕለ ጥብ እስክታደርስ ድረስ በአባት እናቷ ቤት 3 ዓመት ተቀመጠች፡፡ ከመዝ
ነበረት ውስተ ቤተ አቡሃ ወእማ 3ተ ዓመተ እንዘ ትጠቡ ሐሊበ እማ (እንዳለ በነገረ
ማርያም፡፡)
ኢያቄምና
ሐናም
ልጃቸውን
ሲያሰሳድጉና
ስላደረገላቸውም
ሁሉ
እግዚአብሔርን
ፈጽመው
ሲያመሰግኑት
ሦስት
ዓመት
ኖሩ።
በጾም፤
በጸሎት
ተወስነው
ለድሆችና
ለጦም
አደሮች
ምፅዋት
እየሰጡ
በጐ
ሥራ
መሥራትን
አበዙ።
ልጃቸውንም
ድንግል
ማርያምን
በንጽሕና
ሲያሳድጉ
ሦስት
ዓመት
በተፈጸመ
ጊዜ
ሐና
ባሏን
ኢያቄምን
“ወንድሜ
ሆይ
ልጃችንን
ለቤተ
እግዚአብሔር
ብፅዐት
አድርገን
እንስጥ።
ልጃችን
ቤተ
እግዚአብሔርን
ልታገለግል
እንጂ
በዚህ
ዓለም
እኛን
ልታገለግል
እንዳልተሳልን
አስብ
አለችው።”
ኢያቄምም
ይህን
ነገር
ከሚስቱ
በሰማ
ጊዜ
ደስ
አለው።
ነብየ
እግዚአብሔር
ዳዊት
ልጄ
ሆይ
ስሚ
እዪ
ጆሮሸንም
አዘንብዪ
ወገንሽን
የአባትሽንም
ቤት
እርሺ
ንጉሥ/ክርስቶስ/
ውበትሽን
/ንጽሐ
ባሕርይሽን/
ወድዶአልና
መዝ
44÷10-11 ብሎ
እንደተናገረ
ለወላጆቿ
የብፅዐት
ልጅ
የሆነችው
ድንግል
ማርያም
ሆዷ
ዘመድ
ሳይወድ
አፏ
እህል
ሳይለምድ
ከእናቷና
ከአባቷ
ተለይታ
ታህሣሥ
ሦስት
ቀን
በሦስት
ዓመት
ወደ
መቅደሰ
ኦሪት
ገብታለች።
በአታ
ለማርያም
ማለትም
የድንግል
ማርያም
ወደ
ቤተ
መቅደስ
መግባት
ማለት
ነው።
ከዚህም በኋላ በ3 ዓመት
ልተተ ሕፃናትን ፈጸመች አበ እመ እያለች ታጫውት ጀመር እነርሱም ከእንግዲህ ወዲህማ ስእለት መብለት ይሆንብን የለምን ወስደን
እንስጥ ብለው ይዘዋት ወደ ቤተ መቅደስ ሲሄዱ ዘካርያስም ሕዝቡን ሰብስቦ ጉባዔ አድርጎ ሲያስተምር ቆያቸው ከዚያውም ደርሰው
እነሆ ተቀበሉን አሏቸው እነርሱም እንቀበላለን ብለው ቢያዩዋት ከፀሐይ 7 እጅ አብርታ ዕንቈ ባሕርይ መስላ ታያቻቸው እነርሱም
እኛ ይህችን የመሰለች ፍጡር ምን እናደርጋታለን ምን እናበላታለን ምን እንጋርድላታለን ብለው ሲጨነቁ ከዚህም መካከል እመቤታችንን
እግዝእትነ ማርያም መንፈሳዊ ረኅብ ተነስቶባት ምርር ብላ አለቀሰች፡፡
ያን ጊዜ መልአኩ ፋኑኤል
በመሶበ ወርቅ ኅብስት ሰማያዊ ፤ በብርሃን ጽዋ ስቴ ሕይወት ይዞ ረቦ ታያቸው ሕዝቡም ዘካርያስን አባታችን ይህ የወረደው ክብር
ላንተ እንደሆነ ተነስተህ ታጥቀህ እጅ ነስተህ ሰግደህ ተቀበል አሉት፡፡ ዘካርያስም እሽ ብሎ እጅ ነስቶ ሰግዶ እቀበላለሁ ብሎ
ሲያይ ወደሰማይ እራቀው መጠቀው፡፡ ከሕዝቡም እያንዳንዱ እየተነሱ እንቀበላለን ብለው ቢያዩ ወደሰማይ ራቃቸው መጠቃቸው፡፡
ከዚህም በኋላ ዘካርያስ
ሐናን ጠርቶ ለናንተ ለእንግዶች የወረደ ክብር እንደሆነ ሕፃኒቱን ይዘሽ ወደዚያ ፈቅ ብለሽ ተቀመጪ አላት፡፡ እርሷም ሕፃኒቱን
ይዛ ወደዚያ ፈቅ ብላ ተቀመጠች፡፡ መልአኩም ከራሳቸው ላይ ረቦ አልወርድም አለ፡፡