ጥቅስ

ጌታዬ
እግዚአብሔር ሆይ
እስከዚህ ያደረስኸኝ
እኔ ማን ነኝ ?
ቤቴስ ምንድር ነው?
2 ሳሙ 7፥18

Wednesday 25 December 2013

አባ መቃርስ


  1. ታላቁ መቃርስ ከመልካምና ቅዱሳን ቤተሰብ ሻብሺር መኑፍ በተባለ አከባቢ ተወለደ። አባቱ አብራግ እናቱ ደግሞ ሳራ ይባላሉ። ወንድ ልጅ አልነበራቸውም። አብራግ በሕልሙ የእግዚአሔር መልአክ መጥቶ ወንድ ልጅ ትወልዳላችሁ ስሙም በምድር ሁሉ የታወቀ እንደሚሆንና ብዙ ደቀ መዛሙርን እንደሚያፈራ ገለጸለት።

    ሕጻኑ ሲወለድ ገና መቃርስ አሉት ...ትጉሙም የተባረከ ማለት ነው።

    ሰይጣን በአንድ ወቅት ለአባ መቃርስ ጠላቶችህ በጣም በዙ ሲለው አባ መቃርስ “ሰው የሰው ጠላት የለውም” አለውና ሰይጣንን አሳፈረው! ዲያቢሎስም ታዲያ የሰው ጠላት ማን ነው? ብሎ አባ መቃርስን ጠየቀው። አባ መቃርስም የሰው ጠላትማ የእለተ አርቡን ሰው አዳምን የፈተነ ፣ ኢዮብን ፣ ዳዊትን ፣ የበቁ አባቶችን በሙሉ የፈተነ አንድ ፍጥረት ነበር፤ ጠላት እሱ ነው! “አንተ ይህን ፍጥረት አታውቀውም እንዴ?” አለው። ዲያቢሎስም ኧረ በጭራሽ ሰምቼ አላውቅም አንዳችም የማውቀው ነገር የለኝም፤ ይገርማል! እንዴት ያለ ጨካኝ ነው አለ ራሱን እየነቀነቀ! አባ መቃርስም አዎ እንዳልከው ጨካኝ ነው፤ ይህን ፍጥረት አለማወቅህ ግን ገርሞኛል። ይገርምሃል እሱ ጨካኝ ብቻ ሳይሆን የፈጠረውን በገዳመ ቆሮንጦስ የፈተነ ደፋርም ጭምር ነው። ጨካኝና ደፋር ቢሆንም በጌታችን ድል ተነስቷልና እኛም ይህችን ጾም ሰሞኑን እየጾምን እኮ ነው አለው። ይህን ግዜ “ዲያቢሎስ ድል ተነስቷል” የሚለውን ቃል ሲሰማ ሽንፈቱ ትዝ አለውና ተቁነጠነጠ።እንዳይታወቅበት ግን “አይ ደፋሩ ጉድ ጉድ! እያለ ማስመሰሉን ቀጠለ። አባ መርቃስም እንዴ አንተ ይህን ካላወቅህ አትጾምም ማለት ነው እንዴ? አለው ፈገግ እያለ። ዲያቢሎስም ጾ… ጾ ….. ም…. ጾም ትንሽ ስለሚያመኝ…. እያለ ሲቀባጥር አባ መርቃስ አሁንም ፈገግ እያለ አይ አንተ የሰው ጠላት የምትሆነው እስከ መቼ ነው? መታመሜን አውቀህ እንዳልጾም ይህን ሁሉ ቀባጠርክ። ገና ስትመጣ ማን እንደሆንክ አውቅ ነበር! ገና እኔን ለመፈተን ስታስብ አውቅ ነበር! አይ ዲያቢሎስ የሰው ጠላት አንተ ብቻ ነህ! በል አሁን የጾም ግዜ ነውና ዞር በል ብሎ ገሰፀው። ዲያቢሎስም ከእርሱ ራቀ። ይህን የአባ መቃርስን ታሪክ ሳነብ አንድ ነገር ትዝ አለኝ፤ “ዲያቢሎስ እንደ ሚያገሳ አንበሳ በዙሪያችሁ ይዞራል በእምነት ሆናችሁ ተቃወሙት ከእናንተም ይሸሻል” የምትለዋ የሐዋርያው መልዕክት ፩ኛ ጴጥሮስ [፭:፰] ይህን በደንብ እንረዳ ሰው የሰው ጠላት የለውም፤ ጠላት ማን ነው? ጠላት ዲያቢሎስ ነው።

Friday 6 December 2013

ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ

  1. ♥በስመ ሥላሴ♥
    “ሳጥናኤል ይማር አለም ይዳን”
    ==> ኢትዮጵያዊት ጻድቅ የእምነት ሴት አርበኛ ጻድቅ ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ <==
    ጌታም ይህን ሁሉ መከራ እንደ መስዋዕት ቆጥሮላት አእላፍ መላእክቱን አስከትሎ መጥቶ በተስፋዋ ያመነውን ቃል ኪዳኗ የተማጸነውን እስከ 10 ትውልድ ድረስ እንዲምርላት ተስፋዋን ነግሯታል።
    ==> “የእግዚአብሔር ዓይኖች ወደ ጻድቃን ጆሮቹም ወደ ጩ...ኸታቸው ናቸውና …. ጻድቃን ጮኹ፥ እግዚአብሔርም ሰማቸው ከመከራቸውም ሁሉ አዳናቸው……የጻድቃን መከራቸው ብዙ ነው፥ እግዚአብሔርም ከሁሉ ያድናቸዋል…ጻድቃንንም የሚጠሉ ይጸጸታሉ። <== ” መዝ.፴፫፥፲፯¬-፳፩ (33፥17¬-21
    ==> ሀገሯ ቡለጋ ቅድስጌ ልዩ ስሙ ጥጥ ምድር አከባቢ ነው። አባቷ ቅዱስ ደረሳኒ እናቷ ቅድስት እሌኒ ይባላሉ። ቤተሰቦች በክብር በስርዓት ቅድሳት መጽሐፍትን ብሉይ ከሐዲሳት እያስተማሩ ባደገችና ለአካለ መጠን (ለአቅመ ሔዋን) ስትደርስ የመኳንንት የመሳፍንት ልጅ ናትና ለንጉስ ባለሟል ለሆኑ ትውልድ ነገዱ ፃሰርጓ ወገን ሲሆን የኢሱስ ሞዓ ልጅ ሠምራ ጊዮርጊስ ለሚባል ደግ ካህን በሕግ በ14 ዓመቷ ዳሯት። ፲፪ ልጆችም ወልዳለች።
    ==> ከመከራዋ ብዛት ከገድሏ ጽናት ሰውነቷ ተበሳስቶ የዓሣ መመላለሻ እስኪሆን ድረስ ከባህሩ ገብታ ወደ ግራና ቀኝ ሳትል ፲፪ ዓመት ጸለየች። በመጨረሻም ጌታ ምን አደርግልሽ ትሽያለሽ?

Sunday 3 November 2013

ምሥጢረ ንስሐ


 ምሥጢረ ንስሐ
ንስሐ ፦ ነስሐ ተፀፀተ ካለው የተገኘ ሲሆን ፤ ንስሐ ማለት በሠሩት ኃጢአት መፀፀት ፣ ማዘን ፣ ወደ እግዚአብሔር ለመመለስ መወሰን ፤ ማለት ነው ። ንስሐ ከዘለዓለማዊ ፍርድ የሚያድን ፤ ዘማዊውን እንደ ድንግል ፤ ሌባውን መጽዋች የሚያደርግ በፊት ከተሠራው ኃጢአት ንጹህ አድርጎ ፤ ከእግዚአብሔር ጋር አንድ የሚያደርግ  ምሥጢር ነው ።
ንስሐ ፦ ከንስሐ በፊት ፣ በንስሐ ጊዜ ፣ ከንስሐ በኋላ፤ ተብሎ  በሶስት ይከፈላል
ከንስሐ በፊት
1 መፀፀት ፤ አንድ ክርስቲያን በድፍረትም ይሁን በስህተት “የሠራው በደል” መጻሕፍት በማንበብ ፣ ከመምህራን ተምሮ ፣ የስብከት ካሴት አዳምጦ ፤ ህሊናው ወቅሶት ፣ ወይም በሌላ በአንድ ምክንያት ስህተት መሆኑን ከተረዳ በኋላ ተፀፅቶ ከእግዚ አብሔር ለመታረቅ (በደሉን ለማስተስረይ) የሚያደርገው ጉዞ ንስሐ ይባላል ። በሠራው በደል ሳይፀፀት ፤ ለጊዜው ህሊናውን ስለረበሸው ብቻ ንስሐ የሚገባ ሰው ፤ ንስሐውን ከጨረሰ በኋላ ወደ ቀደመ ሕይወቱ ሊመለስ ይችላል ። ምክንያቱም ፡ ንስሐ የገ ባው ፡ በሰራው በደል ከልቡ ተፀፅቶ አስቦበት ሳይሆን ፤ በስሜት ተነሳስቶ ነውና ፤ ስሜቱ ሲጠፋ ሥጋዊ ፍላጎቱም ይነሳሳበትና ውሳኔውንም ሊለውጠው ይችላል ።

Sunday 29 September 2013

አቡነ አኖሬዎስ ዘደብረ ጽጋጋ

አቡነ አኖሬዎስ ዘደብረ ጽጋጋ አትም ኢሜይል
መስከረም 13 ቀን 2005 ዓ.ም.

በመ/ር ሳሙኤል ተስፋዬ

anoros gedam 5.jpgአቡነ አኖሬዎስ በ13ኛው መ.ክ.ዘ የነበሩ ኢትዮጵያዊ ጻድቅ ናቸው፡፡ ትልቁ አኖሬዎስ ይሏቸዋል፡፡ የአቡነ ዜና ማርቆስ የእኅት ልጅ ናቸው፡፡ አባታቸው ቄስ ሰላማ እናታቸው ክርስቶስ ዘመዳ ሲባሉ የትውልድ ቦታቸው ምዕራብ ሸዋ ሙገር አካባቢ ልዩ ስሙ ማትጌ በሚባል ቦታ ነው፡፡ ገድለ ዜና ማርቆስ አባቱ ዘርዐ አብርሃም የተባለ የአቡነ ተክለ ሃይማኖት አባት ዘመድ ነበረ ይላል፡፡

ለአቡነ አኖሬዎስ ወላጆቻቸው ያወጡላቸው ስም ናርዶስ ሲሆን በሕፃንነታቸው የዳዊትን ንባብና የመጻሕፍትን ትርጓሜ ከተማሩ በኋላ በወቅቱ ከነበሩበት ግብፃዊ ጳጳስ ዲቁና ተቀበሉ፡፡ በወቅቱ ሐራንኪስ የተባለ የትርጓሜ መጻሕፍትና የዜማ ዐዋቂ በቤታቸው በእንግድነት ለብዙ ጊዜ በቆየበት ወቅት ለአቡነ አኖሬዎስ ዜማና ትርጓሜ መጻሕፍት በሚገባ አስተምሯቸዋል፡፡ በዚህም ምስጢራተ ቤተ ክርስቲያን፣ ዜማና ትርጓሜ መጻሕፍት የበለጠ ለመረዳት ከነበራቸው ፍላጎት አንጻር ወደ ደብረ አስቦ (ደብረሊባኖስ) በመሔድ ከአቡነ ተክለ ሃይማኖት ጋር ተገናኙ፡፡ በደብረ አስቦ (ደብረሊባኖስ) በገዳም ለረዥም ዓመታት ካገለገሉና ከተማሩ በኋላ በአቡነ ተክለ ሃይማኖት እጅ መንኩሰው አባ አኖሬዎስ ተባሉ፡፡

የገዳሙ መነኮሳት በሊቀ ዲያቆንነት መርጠዋቸው ትርጓሜ መጻሕፍትና ዜማ ያስተምሯቸው ነበር፡፡  ትጋታቸውን ያዩት የገዳሙ መነኮሳትም ከአቡነ ተክለ ሃይማኖት በታች የገዳሙ መጋቢ አድረገው መረጧቸው፡፡ በዚያ ዘመን በገዳሙ ወንዶች እና ሴቶች መነኮሳዪያት በአንድነት ይኖሩ ነበር፡፡ ነገር ግን አቡነ አኖሬዎስ አቡነ ተክለ ሃይማኖትን አማክረው የሴትና የወንድ ገዳም እንዲለይ አደረጉ፡፡ ከዚህ በኋላ በወቅቱ በነበሩት አቡነ ቄርሎስ ዘንድ ተልከው ቅስናን ተቀበሉ፡፡

Wednesday 31 July 2013

ትምህርተ ጋብቻ ክፍል ፫ (3)

ከ መልአከ ሰላም ቀሲስ ደጀኔ ሺፈራው ብሎግ የተወሰደ
፩፦ መጠናናት፤
            ምንም እንኳን የሰው ልጅ ተጠንቶ የማያልቅ ሳይንስ ቢሆንም ፦ ወደ ትዳር ዓለም ከመግባት በፊት ፦እንደ ሰው፥ በሰው አቅም መጠናናት እንደሚያስፈልግ ለማንም ግልጥ ነው። ይኸውም በሰከነ ልቡና ፥ በተረጋጋ መንፈስ ሊሆን ይገባል። በትውውቅ ሰሞን የተሸፈነ ብዙ ነገር ፥ በሂደት ቀስ እያለ ብቅ ማለቱ ስለማይቀር ጊዜ መስጠት ያስፈልጋል። ሰውን የምናጠናው ድካም የሌለበት ፍጹም የሆነ ሰው ለማግኘት አይደለም። ምክንያቱም እኛም ፍጹም አይደለንምና ነው ፥ አንድም በዓለመ ሥጋ ፍጹም ሰው አይገኝምና ነው። በመሆኑም፦ በእኛ ዘንድ ድካም እንዳለ ሁሉ ፦ በሌላም በኲል ድካም ሊኖር እንደሚችል አምነን ኅሊናችንን ልናዘጋጀው ይገባል። ከዚ ህ በኋላ ድካሙን ፦ በአራት ደረጃ ከፍለን ልናየው እንችላለን። ፩ኛ፦ በቶሎ የሚወገድ ድካም ፤ ፪ኛ ፦ በሂደት የሚወገድ ድካም፤ ፫ኛ፦ ልንሸከመው የሚገባን ድካም፤ ፬ኛ ፦ የማይወገድ ድካም፤
፩፥፩፦ በቶሎ የሚወገድ ድካም፤
            የሰው ልጅ በትምህርት ፥ በምክርና በተግሣጽ ፦ ከጥፋቱ ሊመለስ ፥ ከድካሙም ሊበረታ ይችላል። ስለሆነም ያሉትን ደካማ ጐኖች ዘርዝሮ በማውጣት ፦ እርስ በርስ መነጋገር ፥ መማማር ያስፈልጋል። ከአቅም በላይ የሆነውን ደግሞ ወደ ካህኑ በማምጣት ማስ መከር ይገባል። እንዲህ ዓይነቱ ድካም ፦ ከእውቀት ማነስ፥ ከመካሪ ማጣት ፥ አርአያ የሚሆን ሰው ካለማግኘት በመሆኑ በቶሎ ይወ ገዳል። ጠቢቡ ሰሎሞን፦ «ምክር በሰው ልቡና እንደ ጥልቅ ውኃ ነው፤ አእምሮ ያለው ሰው ግን ይቀዳዋል።» እንዳለ፦ አእምሮ ያላቸው የሚያስተውሉ ሰዎች ይስተካከሉበታል። ምሳ ፳፥፭። «ተግሣጽን የሚወድድ ዕውቀትን ይወድዳል፤» እንዲል፦ በሁሉ ይገሠጻሉ። ምሳ ፲፪፥፩። «የተማረ ልጅ ብልህ ይሆናል፤» እንዲል፦ ልባሞች ፥ አስተዋዮች እየሆኑ ይሄዳሉ። ምሳ ፲፥፭። ይህም ከምድራዊ ሀብት የሚበልጥ ሀብት ነው። ምክንያቱም « ከብር ይልቅ ትምህርትን ፥ ከተፈተነ ወርቅም ይልቅ ዕውቀትን ተቀበሉ ፤ » ይላልና። ምሳ ፰፥፲። «ትምህርትና ተግሣጽም የሕይወት መንገድ ነውና፤» የሚልም አለ። ምሳ ፮፥፳፫።

ትምህርተ ጋብቻ፡- ክፍል ፪ (2)


 ከ መልአከ ሰላም ቀሲስ ደጀኔ ሺፈራው ብሎግ የተወሰደ



፩፡- የትዳር ጓደኛን ማን ይምረጥልን?

          የትዳር ጓደኛ በሰው ልጅ ሕይወት ውስጥ መሠረታዊ ጉዳይ ነው። ባለጸጋ ፥ወይም ባለሥልጣን፥ ወይም ቆንጆ፥ ወይም ጤነኛ፥ ስለሆኑ ብቻ የሚሹት አይደለም። ደሀ፥ ወይም ተርታ ሰው፥ ወይም መልከ ጥፉ፥ ወይም በሽተኛ ፥ቢሆኑም የሚፈለግ የሚናፈቅ ነው። ሳያገቡ ለመኖር የወሰኑትም ቢሆኑ ፥ፍላጎቱ ያለው በአፍአ ሳይሆን በውስጥ ስለሆነ፥ ከኅሊና ውጣ ውረድ ሊድኑ አይችሉም። ስለሆነም ከኅሊናቸውና ከፍላጎታቸው ጋር እየታገሉ በገድል ይኖራሉ። በዚህ ትግል ማሸነፍም መሸነፍም ሊኖር ይችላል። የትዳር ጓደኛ ከውጭ ወደ ውስጥ የምናስገባው ሳይሆን፥ ከውስጣችን ፈልገን የምናገኘው ነው። ይህም ማለት፡- በአዳምና ሔዋን ሕይወት እንዳየነው፡- እግዚአብሔር የትዳር ጓደኞቻችንን አስቀድሞ በእያንዳንዳችን ሕይወት ውስጥ አስቀምጧቸዋል። በመሆኑም አንድ ሰው ሥዕል (ፎቶ ግራፍ) ይዞ የሥዕሉን ባለቤት እንደሚፈልግ በውስጣችን የተቀመጠውን፥ የተሣለውን ይዘን መፈለግ ይገባል።

የሰው ልጅ በእምነቱም ሆነ በሌላው ነገር ሁሉ ፍጹምነት ስለሌለው በፍለጋው (በመንገዱ) አጋዥ ያስፈልገዋል። ያንንም የሚሰጠን ያለ ጥርጥር እግዚአብሔር ነው። ለዚሀም የጾምና የጸሎት ሰው መሆን ያስፈልጋል። የነቢያት አለቃ ሙሴ ጽላቱን ከእግዚአብሰሔር እጅ የተቀበለው አርባ መዓልትና አርባ ሌሊት ጾሞ ነው፥ እንጀራ አልበላም፥ ውኃም አልጠጣም። ዘጸ ፴፩፥፲፰። እኛም እንደ ጽላት እንደ ታቦት ተከብረው የሚያስከብሩ የትዳር ጓደኞቻችንን በጾምና በጸሎት ልናገኛቸው እንችላለን ብለን ልናምን ይገባል። በአገራችን፡-«አቶ እገሌ እኮ ታቦት ማለት ናቸው፥ ወ/ሮ እገሊት እኮ ታቦት ማለት ናቸው፤» የሚባሉ ነበሩ። ታቦት የሚያሰኛቸው የጸና ሃይማኖታቸው፥ የቀና ምግባራቸው ነበረ።

ትምህርተ ጋብቻ ክፍል ፦ ፩

    ከ መልአከ ሰላም ቀሲስ ደጀኔ ሺፈራው ብሎግ የተወሰደ
http://www.betedejene.org/2010/12/blog-post.html
፩፦ « መጋባት በሁሉ ዘንድ ክቡር ነው፤» ዕብ ፲፫፥፬
          ጋብቻን ባርኮና ቀድሶ ለሰው ልጅ የሰጠው እግዚአብሔር ነው። በመሆኑም ጋብቻ የእግዚአብሔር ጸጋ ነው። ስለዚህ በዓይን ምኞት ተጋርደው፥ በሥጋ ፍላጐት ተነድተው ፥ በስሜት ፈረስ ጋልበው ፥ የሚገቡበት ሳይሆን ፦ በጸሎት እና በምልጃ ፈቃደ እግዚአብሔርን ጠይቀው የሚፈጽሙት ታላቅ ምሥጢር ነው።
          ጋብቻ የሰው ሁሉ ሕልም ነው። የማይመኘው፥የማይፈልገው የለም። የሰው  ሁሉ ጸሎት፥ የሰው ሁሉ ስእለት ነው። ለመሆኑ፦ ህልሙ የተፈታለት ፥ ጸሎቱ የደረሰለት ፥ ስዕለቱ የሰመረለት ስንቱ ይሆን? ያላገባው ይናፍቃል ፥ ያገባው ደግሞ ያማርራል። ከጋብቻ በፊት « መልአክ » የተባለ የትዳር ጓደኛ ከጋብቻ በኋላ «ሰይጣን» ይባላል። «እኔ የመረጥኩትን ካላገባሁ እሰቀላለሁ፤» እንዳልተባለ «ካልተፋታሁ መርዝ እጠጣለሁ፤» ለማለት ችግር የለም። ከጋብቻ በፊት ምክር ላለመስማት አሳብ ላለመቀበል፦ «ስለ እኔ ማንም አያገባውም፤» ተብሎ በር እንዳልተዘጋ ሁሉ ከጋብቻ በኋላ ግን ጣልቃ የማያስገቡት ሰው  የለም ፤ «ምን በወጣህ ፥ ምን በወጣሽ፤» የሚለውን ፈጥኖ ለመቀበል በሩ ለሁሉም ክፍት ነው።
፪፦ ጋብቻ እንዴት ተጀመረ?

          ጋብቻ በአዳምና በሔዋን እንደተጀመረ የጎላ፥ የተረዳ ፥ የታወቀ ነገር ነው። «ተባዕተ ወአንስተ ገብሮሙ፤ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው፤ » እንዲል፦ አዳም ሲፈጠር ሔዋን በውስጡ ነበረች። ዘፍ ፩፥፳፰። ይህም በባህርዩ ነበረች ማለት ነው። አንድ አካል፥ አንድ ሥጋ ከሚያሰኛቸው ምሥጢር አንዱና ዋነኛውም ይኸው ነው።
          ጋብቻ የተጀመረው በአዳም ጥያቄ ነው፤ ጥያቄዎም የኅሊና ማለትም ውሳጣዊ ነበር። ምክንያቱም፦ ከላይ እንደተ መለከትነው፦ የትዳር ጓደኛው በውስጡ ስለነበረች ነው። « እግዚአብሔር አምላክም፦ ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም፤ የሚመቸውን ረዳት እንፍጠርለት፥አለ፤»ይላል። እግዚአብሔር እንዲህ ማለቱ፦ በአዳም ኅሊና ውስጥ ይህ ጥያቄ እንደሚነሣ ስለሚያውቅ ነው። መናገሩም ለአዳም ኅሊና እንጂ ፥ ሔዋን ለአዳም እንደምትፈጠርለት አስቀድሞ በእግዚአብ ሔር ዘንድ የተወሰነ ነው።

Tuesday 11 June 2013

ምን ዓይነት ጸሎት በየትኛው ሰዓት ልጸልይ?

ምን ዓይነት ጸሎት በየትኛው ሰዓት ልጸልይ?

መልስ-ጸሎት በክርስትና ሕይወት እጅግ አስፈላጊ መሆኑ ጥያቄ የለዉም፡፡በዚህ ጽሑፍ የምንጸልይባቸውን ጊዜያት፣የምንጸልየውን የጸሎ ት ዓይነት፣ ለመመልከት እንሞክራለን፡፡

1. የጸሎት ጊዜያት

... ልበ አምላክ ነቢየ ልዑል ቅዱስ ዳዊት”ስብዓ ለእለትየ እሴብሐከ በእንተ ኵነኔ ጽድቅከ ፣ስለ ጽድቅህ ፍርድ በቀን ሰባት ጊዜ አመሰግንሃለው”/መዝ 118-164/ብሎ እንደተናገረ ክርስቲያን የሆነ ሁሉ ሰባት ጊዜ በየእለቱ እንዲጸልይ ቤተ ክርስቲያን ታስተምረናለች፡፡ሰባቱ የጸሎት ጊዜያትም የሚከተሉት ናቸው፡፡

1.1 ጸሎተ ነግህ

ቅዱስ ዳዊት “አምላኬ አምላኬ በማለዳ ወደ አንተ እገሰግሳለሁ” መዝ 62÷11 እንዳለ ሌሊቱ አልፎ ቀኑ ሲተካ፣ከመኝታችን ስንነሳ ምንጸልየው የጸሎት ዓይነት ጸሎተ ነግህ ይባላል፡፡በዚህ ጊዜ የሚከተሉትን ምስጢራት እያሰብን መጸለይ ይገባናል፡፡
==>ሌሊቱን አሳልፎ ቀኑን ስለተካልን እያመሰገንን ወጥተን እስክንገባ በሰላም ጠብቆ ውሎአችንን የተባረከ እንዲያደርግልን እንጸልያለን።
==>የመጀመሪያው ሰው አዳም የተፈጠረበትም ሰዓት በመሆኑ ያንን እያሰብን እንጸልያለን፡፡
==>የሰውን ልጅ በመዓልትና በሌሊት የሚጠብቁ መላእክት ለተልዕኮ ሲፋጠኑ የሚገናኙበት ሰዓት ነው፡፡የሌሊቱ መልአክ ሲሄድ የቀኑ መልአክ ሲቀርብና ሲተካ የሚገናኙበት በመሆኑ በዚህም ሰዓት እንጸልያለን፡፡
==>ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ሰው ልጆች በደል በጲላጦስ አደባባይ የቆመበት ሰዓት በመሆኑ
እንጸልያለን።

1.2 ጸሎተ ሠለስት (3 ሰዓት)

የጌታችን የእየሱስ ክርስቶስ እናት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም መስቀሉ ስር


††† የጌታችን የእየሱስ ክርስቶስ እናት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም መስቀሉ ስር ቆማ ሆድን መሚያቃጥል አንጀትን በቢቆራርጥ በጽኑ ሃዘን ታለቅስ ታነባ ነበር፤

††† በድንግልና ስለፅነሰችው በድንግልና ስለወለደቸዉ ልጅዋ ድንግል ማርያም ለምን አታለቅስ፤
††† ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በማህጽንዋ ሰለተሸከመችዉ ልጅዋ ድንግል ማርያም ለምን አታለቅስ፤
††† በድን...ግልና ስላጠባችው ልጅዋ ድንግል ማርያም ለምን አታለቅስ፤
††† ከሃገር ሃገር ተጉዛ በግብጽ በራሃ ስለተንከራተተችበት ልጅዋ ድንግል ማርያም ለምን አታለቅስ፤
††† ራሄል ለልጆችዋ የምታለቅስ ከሆነ ድንግል ማርያም ስለተወደደዉ ልጅዋ ለምን አታለቅስ፤
††† ራሄል ከአንድ ቦታ ወደአንድ ቦታ ይዛቸዉ ላልተሰደደቻቸዉ ልጅዎችዋ የምታለቅስ ከሆነ ድንግል ማርያም በስደትና በሰቃይ ወደ በረሃ ይዛው ለተሰደደችዉ ልጅዋ ልምን አታለቅስ፤
††† መቃብራቸዉን ላላየችው ልጅዎችዋ ራሄል የምታለቅስ ከሆነች ድንግል ማርያም የታተመ የልጅዋን መቃብር እያየች ለምን አታለቅስ፤
††† የ12 ነገድ አባት ሽማግሌዉ ያእቆብ ስለልጁ ስለዮሴፍ ያለቀሰዉ ለቅሶ ዛሬ አዲስ ሆኖ ተገኜ፤
††† ያእቆብ ልጁ ዮሴፍን ወንድሞቹ ሲያስሩት አላየም ድንግል ማርያም ግን ልጇ በመስቀል ላይ ተቼንክሮ አይታዋለች፤
††† ያእቆብ ወንድሞቹ ዮሴፍን ከጉድጋድ ሲጥሉት አላየም ፤ ድንግል ማርያም ግን በአይሁድ አደባባይ ልጇ ተሰቅሎ አይታዋለች፤
††† ያእቆብ ወንድሞቹ ልብሱን ገፈው ሲሼጡት አላየም ፤ ድንግል ማርያም ግን ይሁዳ ልጇ በ30 ብር ሲሸጡት አይታለች፤
††† ያእቆብ በልጁ ደም ሳይሆን የበግ ደም አይቶ ነዉ ያለቀሰዉ ፤ መለኮት የተዋሃደዉ የክርስቶስ ደም ግን ድንግል በምታለቅስበት አለት ላይ ፈሰሰ ፤ ስለዚህ አለቀሰች ፤

ስለተወደደ ልጇ ድንግል ለምን አታለቅስ†††


††† ሰባቱ የመላእክት አለቆች መጥተዉ አረጋግዋት ፤ አጽናንዋት እርሷ ግን በመስቀል ላይ የተሰቀለዉ ልጇ እያየች ለቅሶ መተዉን መጽናናትም አልተዎችም፤
††† አባትዋ ዳዊት እሳት በሆነ ፈረስ መጥቶ አጽናናት እርሷ ግን ለቅሶ መተዉን አልቻለችም ፤ እስከ ሶስት ቀን ድረስም እህል ውሃ አላለችም፤

Sunday 28 April 2013

+++በብሉይ ኪዳን ውስጥ ካሉ ስሞች ከነትርጓሜያቸው በጥቂቱ++


+++በብሉይ ኪዳን ውስጥ ካሉ ስሞች ከነትርጓሜያቸው በጥቂቱ++

 ፩። ዮሃንስ ፡፡ የእግዚአብሔር ፀጋ (ሀሴት፣ ፍስሀ)

፪። ዳንኤል ፡፡ እግዚአብሔር ፈራጅ ነው

፫። ኤልሳእ ፡፡ እግዚአብሔር ደህንነት

፬። አሞን ፡፡ የወገኔ ልጅ

፭። እስራኤል ፡፡ የእግዚአብሔር ህዝቦች

፮። ማሪያም ፡፡ የእግዚአብሔር ስጦታ

፯። ሀና ፡፡ ፀጋ

፰። ሩሀማ ፡፡ ምህረት የሚገባት

፱። እያሱ ፡፡ እግዚአብሔር አዳኝ ነው፣ መድሃኒት

፲። ጌርሳም፡፡ ከሌላ ምድር ስደተኛ ነኝ

፩፩። እዮሳፍጥ፡፡ እግዚአብሔር ፈርዷል

፩፪። እዮአም ፡፡ አዳኝ

+++በብሉይ ኪዳን ውስጥ ካሉ ስሞች ከነትርጓሜያቸው በጥቂቱ++


+++በብሉይ ኪዳን ውስጥ ካሉ ስሞች ከነትርጓሜያቸው በጥቂቱ++

 ፩። ዮሃንስ ፡፡ የእግዚአብሔር ፀጋ (ሀሴት፣ ፍስሀ)

፪። ዳንኤል ፡፡ እግዚአብሔር ፈራጅ ነው

፫። ኤልሳእ ፡፡ እግዚአብሔር ደህንነት

፬። አሞን ፡፡ የወገኔ ልጅ

፭። እስራኤል ፡፡ የእግዚአብሔር ህዝቦች

፮። ማሪያም ፡፡ የእግዚአብሔር ስጦታ

፯። ሀና ፡፡ ፀጋ

፰። ሩሀማ ፡፡ ምህረት የሚገባት

፱። እያሱ ፡፡ እግዚአብሔር አዳኝ ነው፣ መድሃኒት

፲። ጌርሳም፡፡ ከሌላ ምድር ስደተኛ ነኝ

፩፩። እዮሳፍጥ፡፡ እግዚአብሔር ፈርዷል

፩፪። እዮአም ፡፡ አዳኝ

Sunday 14 April 2013

ለመፅሀፍ ቅዱስ ጥናት የሚያስፈልጉ መንፈሳዊ መርሆዎች

Photo: ለመፅሀፍ ቅዱስ ጥናት የሚያስፈልጉ መንፈሳዊ መርሆዎች

1.መፅሀፍ ቅዱስን ማክበርና በተሰበረ ልብ ማጥናት ያስፈልጋል:: ኢሳ.66:2. 57:15
2. የመፅሀፍ ቅዱስን ጥቅምና ዋጋ በመረዳት ማጥናት:: 2ጢሞ.3:15-17, መዝ.119:105, 29:3-9
3. በእግዚአብሄር መንፈስ መሪነትና አብሪነት ማጥናት:: 1ቆሮ.2:11 1ዮሀ.2:20-21:27
4. ለመፅሀፍ ቅዱስ ከፍተኛ ፍቅር ሊኖር ይገባል:: መዝ.119:47-48,97
5. በፀሎት መንፈስ ማጥናት ያስፈልጋል::ሉቃ.24:44, መዝ.119:17,ቆላ.4:3-4,ኤፌ.6:18:-20
6. በመታዘዝ መንፈስ ማጥናት ያስፈልጋል:: መዝ.119.166-168 ያእ.1:22
7. በትጋት ዘወትር ሳያቁዋርጡ ማጥናት ያስፈልጋል:: መዝ.1:2, 119:123, ኢያሱ.1:8, ዘዳ.17:18-20
8. በጥማትና በናፍቆት ማጥናት:: መዝ.119:40,131, ማቴ.5:6
9. ንፁህ ልብና ህይወት ያስፈልጋል:: ህዝ.18:30-31, እብ.12:14, ዘፀ.19:10-11
10. በተዘጋጀና ንቁ አእምሮና መንፈስ ማጥናት ያስፈልጋል:: ፊሊ4:6-7
11. በሙሉ ልብና መንፈስ ማጥናት ያስፈልጋል:: ኤር.29:13, መዝ.119:69
12. ፀጥተኛና አመቺ ቦታ ማዘጋጀት. ኢሳ.30:15
13. በዝግታና በማስተዋል ማንበብብ.
14. እግዚአብሄር በቃሉ እንደሚናገረን መጠበቅ. ራኢይ.3:7, መዝ.85:8
15. የተወሰነ የመፅሀፍ ቅዱስ ክፍል መጥኖ ማንበብ.
16. ያልተረዱት ክፍል ሲገጥም የሌሎችን እገዛ መጠየቅ. ሀዋ.8:30-31
17. የተረዱትን እውነት ባማስታወሻ መያዝ
18. ያነበቡትን ክፍልና መልእክቱን ማሰላሰል. መዝ.119:15-16, 97:99
19. መልእክቱን በህይወታችን ውስጥ ተግባራዊ ለማደረግ መጣጣር. መዝ.119:133, ያእ.1:22-25
20. መልእክቱን ለለሎች ማካፈል. እዝ.7:10, ሮሜ.10:10, ገላ.6:6 

መፅሀፍ ቅዱስን የማንበብብ ጥቅም

1. ነፍሳችንን ያድናል ያእ.1:21, 1ጢሞ.4:16, ሮሜ. 1:16, 2ቲሞ.3:15
2. መንፈሳዊ ህይወትን ያሳድጋል (በእምነት በፍቅር በፀጋና ኢውቀት ወ ዘ ተ..) 1ጴጥ.2:2-3, 2ኛ ጴጥ.3:18 ቆላ, 1:9-12, ፊል.1:9-11, 1ኛተሰ.1:2-3, 2ኛ ተሰ.1:3, ፊል4:7
3. ህይወታችንን ያንፃል ይቀድሳል መዝ.(119):9, ዮሀ.15:3, ኤፌ.5:26 ኢሳ.52:11
4. እውነተና የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዝሙር ወይም ተከታይ ያደርጋል ዮሀ.8:31, ሉቃ.6:40 ማቴ.28:19.20
5. እግዚአብሄርን እንዳንበድል ወይም ሀጢአትን እንዳንሰራ ይገስፀናል መዝ(119):11, 1ቆሮ.10:11 2ጢሞ.3.16:-17, ምሳ.3:11-12, መዝ(141):5
6. ከመለኮት ባህሪ ተካፋዮች በተስፋ ቃል እንድንሆን ያደርጋል 2ጴጥ.1:2-4
7. በነፃነት እንድንኖር ወይም ከሀቲአት ባርነት ነፃ እንድንወጣ ያደርጋል ዮሀ.8:31-32, ያእ.1:25, ገላ 5:1
8. እምነት እንዲኖረን ያደርጋል ሮሜ.10:17, እብ.4:2
9. ጥበብንና ማስተዋልን ማግኘት እንድንችል ያደርጋል መዝ.(119):130 መዝ(19):7, መዝ(119):98.100, መሳ.2:1-6 ምሳ.1:2-7, 20-22
10. የሚያጠነክረንና የሚያፀናን ቃል ስለ ሆነ ኢዩ.17:9, መዝ(119):28, ሀዋ.20:32
11. ክፉውን ሁሉ ለማሸነፍ ብርታትን የሚሰጠን ቃል ስለ ሆነ. 1ዮሀ.2:14, ኤፌ.6:13-17
12. የእግዚአብሄርን ሰው ፍፁምና ለበጎ ስራ ሁሉ የተዘጋጀ እንዲሆን ያደርጋል. 2ጢሞ.3:16-17 1ጴጥ.3:15
13. የእግዚአብሄር ቃል ዲያቢሎስን ማሸነፍ ያስችላል.ማቴ.4:1-11, ኤፌ.6:10-18
14. በእግዚአብሄር ፊት የማያሳፍር ሰራተና ሆኖ ለመገኘት በቃሉ መታጠቅ ወይም ቃሉን በትጋት ማጥናት ስለሚያስፈልግ . 2ጢሞ.2:15, መዝ(105):19
15. በመከራችን ጊዜ መፅናናትን ተስፋን ስለሚሰጠን መዝ(119):50, መዝ(55):22, ሮሜ.15:4
16. አእምሮን ሁሉ የሚያልፍ የእግዚአብሄር ሰላም የሚገኘው በቃሉ በመኖር ብቻ ስለሆነ መዝ(119):165, ኢሳ.48:17,-19, ኢሳ.54:13, ዮሀ.14:2
17. ለእግራችን መብራት ለመንገዳችንም ብርሀን የሚሆን ቃል ወይም መለኮታዊ ምሪትን የምናገኝበት ቃል ስለሆነ መዝ(119):130, ምሳ.6:23
18. ፈታኝ ሁኔታ ሲያጋጥመን ምላሽ ለመስጠት መዝ.(119)43, ሉቃ. 12:11-12, 1ጴጥ.3:15, ዮሀ.14:26
19. ቃሉ በክፉዎች መናፍስት ላይ ትልቅ ስልጣን ስላለው ማቴ.8:16-17, 8:8, 4:23-25, 15:29-31
20. በህይወታችን ማእበል (ነፋስና ጎርፍ) ሲነሳ እንዳንናወጥ ያደርጋል:: ማቴ.7:24-27, ሉቃ.6:46-49, 1ቆሮ.16:13, 15:58, ኤፌ.4:14-16
21. በቃሉ እውቀት መሞላት የሀሰት ትምህርቶችን ለመከላከልም ሆነ ለማፍረስ ወሳኝ ስለሆነ. ኤር.1:9-10, 23:16-18, ቁጥ.25-32, ዘዳ.13:1-5, ሀዋ.20:29-32, ማቴ.7:14-15, ሮሜ.16-17 -18, 2ጴጥ.2:1-3, 1ዮሀ.4:1-6, 2ዮሀ.7:11
22. ለፀሎታችን መልስ ለማግኘት ያስችለናል. 1ዮሀ.3:
ለመፅሀፍ ቅዱስ ጥናት የሚያስፈልጉ መንፈሳዊ መርሆዎች

1.መፅሀፍ ቅዱስን ማክበርና በተሰበረ ልብ ማጥናት ያስፈልጋል:: ኢሳ.66:2. 57:15
2. የመፅሀፍ ቅዱስን ጥቅምና ዋጋ በመረዳት ማጥናት:: 2ጢሞ.3:15-17, መዝ.119:105, 29:3-9
3. በእግዚአብሄር መንፈስ መሪነትና አብሪነት ማጥናት:: 1ቆሮ.2:11 1ዮሀ.2:20-21:27
4. ለመፅሀፍ ቅዱስ ከፍተኛ ፍቅር ...ሊኖር ይገባል:: መዝ.119:47-48,97
5. በፀሎት መንፈስ ማጥናት ያስፈልጋል::ሉቃ.24:44, መዝ.119:17,ቆላ.4:3-4,ኤፌ.6:18:-20
6. በመታዘዝ መንፈስ ማጥናት ያስፈልጋል:: መዝ.119.166-168 ያእ.1:22
7. በትጋት ዘወትር ሳያቁዋርጡ ማጥናት ያስፈልጋል:: መዝ.1:2, 119:123, ኢያሱ.1:8, ዘዳ.17:18-20
8. በጥማትና በናፍቆት ማጥናት:: መዝ.119:40,131, ማቴ.5:6
9. ንፁህ ልብና ህይወት ያስፈልጋል:: ህዝ.18:30-31, እብ.12:14, ዘፀ.19:10-11
10. በተዘጋጀና ንቁ አእምሮና መንፈስ ማጥናት ያስፈልጋል:: ፊሊ4:6-7
11. በሙሉ ልብና መንፈስ ማጥናት ያስፈልጋል:: ኤር.29:13, መዝ.119:69
12. ፀጥተኛና አመቺ ቦታ ማዘጋጀት. ኢሳ.30:15
13. በዝግታና በማስተዋል ማንበብብ.
14. እግዚአብሄር በቃሉ እንደሚናገረን መጠበቅ. ራኢይ.3:7, መዝ.85:8
15. የተወሰነ የመፅሀፍ ቅዱስ ክፍል መጥኖ ማንበብ.
16. ያልተረዱት ክፍል ሲገጥም የሌሎችን እገዛ መጠየቅ. ሀዋ.8:30-31
17. የተረዱትን እውነት ባማስታወሻ መያዝ
18. ያነበቡትን ክፍልና መልእክቱን ማሰላሰል. መዝ.119:15-16, 97:99
19. መልእክቱን በህይወታችን ውስጥ ተግባራዊ ለማደረግ መጣጣር. መዝ.119:133, ያእ.1:22-25
20. መልእክቱን ለለሎች ማካፈል. እዝ.7:10, ሮሜ.10:10, ገላ.6:6

የድንግሊቱ ስም››


‹‹የድንግሊቱ ስም››

በዚህ አጠር ያለ ጽሑፍ ውስጥ የእመቤታችንን ስም አጠራሯን ብቻ የሚመለከቱ በአጠቃላይ ሦስት መሠረታዊ ነጥቦችን እንዳስሳለን፡፡

እመቤታችን በብሉይ ኪዳን አበው ሁሉ ዘንድ በብዙ ትንቢቶችና በብዙ ኅብረ አምሳል ትነገር ነበር፡፡ በአዲስ ኪዳን ግልጥ ባለ መልኩ ለመጀመሪያ ጊዜ የተጠቀሰችው ቅዱስ ሉቃስ ስለ ብሥራተ መልአክ በተረከበት አንቀጽ ነበር፡፡ መተዋወቅ... ከስም የሚጀምር በመሆኑ ቅዱስ ሉቃስ በወንጌሉ ‹‹የድንግሊቱም ስም ማርያም ነበረ›› ሲል የእመቤታችንን ስመ ተጸውዖ በመግለጥ ለዓለም ሁሉ ያስተዋውቃታል፡፡ (ሉቃ1.27)

1ኛ. ስሟ የተለየ ስለመሆኑ

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በብሉይና በአዲስ ኪዳን ማርያም በሚለው ስም የተጠሩ ከስምንት የማያንሡ ሴቶች አሉ፡፡ የሙሴ እኅት ማርያም፣ ባለሽቱዋ ማርያም፣ መግደላዊት ማርያም፣ የቀለዮጳ ሚስት ማርያም፣ …እያሉ የሁሉንም መጠቀስ ይቻላል፡፡ ነገር ግን አንዳቸውም ከድንግል ማርያም ወላዲተ አምላክነት በኋላ የተሰየሙ አይደሉም፡፡ ማርያም በሚለው ስም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሱ ሴቶች ሁሉ በእርሷ ዘመንና ከእርሷ በፊት የተሰየሙ ናቸው፡፡ ነገር ግን የእቤታችን ክብርና ማዕርግ /ደረጃ/ ይፋ ከሆነ በኋላ ማለትም የአምላክ እናትነቷ ከተገለጠ በኋላ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የተጠራች አንዲትም ሴት የለችም፡፡

Saturday 16 March 2013

አርባ መአልትና አርባ ሌሊት ጾመ ማቴ.4፥2

አርባ መአልትና አርባ ሌሊት ጾመ ማቴ.4፥2 አትም ኢሜይል

የካቲት 29/2004 ዓ.ም.
በመ/ር ምሥጢረሥላሴ ማናየ
ይህ ከላይ ያነሣነው ርዕስ ክብር ምስጋና ይግባውና ጌታችንና አምላካችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አርባ መአልትና አርባ ሌሊት መጾሙን ያስተምረናል፡፡
በዚህ ኀይለ ቃል ሁለት ታላላቅ ቁም ነገሮችን ቃላትን እንመለከታለን
  1. አርባ መአልትና አርባ ሌሊት
  2. ጾም የሚሉት ናቸው፡፡

በቅድሚያ አርባ መአልትና አርባ ሌሊት የሚለውን ከእነ ምስጢሩ እንመለከተዋለን፡፡ ቀጥለን ደግሞ ጌታችንስ ለምን አርባ መአልትና አርባ ሌሊት ጾመ? የሚለውን እንመለከታለን እግዚአብሔር አይነልቡናችንን ይክፈትልን፡፡

እግዚአብሔር አምላካችን የፈጠረውን የሰው ልጆችን አባት አዳምን፣ በልጅነት አክብሮ ገነት ያስገባው በፈጠረው በአርባ ቀኑ ነው፡፡ “ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ እግዚአብሔር ዘገብሮ ለአዳም” አዳምን የፈጠረ እግዚአብሔር ቅዱስ ነው እያሉ እያመሰገኑ መላእክት ወደገነት አስገብተውታል /ቀሌ.4፥/

“ወላምድኅረ ተፈጸመ ለአዳም ፵ መዋዕል በምድር ኀበ ተፈጥረ አባዕናሁ ውስተ ገነተ ኤዶም ኩፋ.9፥12 ለአዳም አርባ ቀን ከተፈጸመለት በኋላ ወደገነት አስገባነው፡፡ ሔዋንንም በሁለት አርባ ማለትም በሰማኒያ ቀኑዋ ወደገነት አስገቧት ኩፋ.4፥12

በተጨማሪም አዳም ትእዛዘ እግዚአብሔር ካፈረሰ በኋላ ዲያብሎስ በአቋራጭ መጥቶ አስወጣው እንጂ ሱባኤ የገባው ለአርባ ቀናት ነበር፡፡ ይህን አርባ ቀን የሰው ልጆች ከስህተት በኋላ በቀንም ሆነ በዓመት ለጾም፣ ለሱባኤ፣ ከዚያ አልፎ ለመቅጫነት አግልሏል፡፡

Monday 11 March 2013

ወደ ቤቴል ውጣ በዚያም ኑር ዘፍ.35፥1

ወደ ቤቴል ውጣ በዚያም ኑር ዘፍ.35፥1 አትም ኢሜይል

የካቲት 27 ቀን 2005 ዓ.ም.
ዲ/ን ሰለሞን መኩሪያ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ
ይህንን የተናገረ አምላካችን እግዚአብሔር ነው፡፡ ይህ የተነገረው እስራኤል ለተባለ ያዕቆብ ነው፡፡
በቅዱስ መጽሐፍ ታሪኩ ተጽፎ እንደምናገኘው ከወንድሙ ከዔሳው ሸሽቶ የአባቱን የይስሐቅን በረከት ተቀብሎ ወደ አጎቱ ወደ ላባ ሲሄድ ሎዛ ከምትባለው ምድር ሲደርስ ጊዜው መሸ፡፡ እርሱም ደክሞት ስለነበር ድንጋይ ተንተርሶ ተኝቶ ሳለ ሌሊት በራእይ እግዚአብሔር ተገለጠለት ራእዩም የወርቅ መሰላል ከምድር እስከ ሰማይ ተተክሎ በመሰላሉ መላእክት ሲወጡ ሲወርዱ ነበር፡፡ እግዚአብሔርም በዙፋኑ ተቀምጦ ነበር፡፡ ያዕቆብንም “እኔ የአብርሃም አምላክ የይስሐቅ አምላክ እግዚአብሔር ነኝ፤ አትፍራ፣ ይህችን አንተ የተኛህባትን ምድር ለአንተም ለዘርህም እሰጣለሁ ዘርህም እንደ ባሕር አሸዋ ይሆናል፡፡ በአንተ በዘርህ አሕዛብ ይባረካሉ፡፡ እነሆም እኔ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፡፡ የነገርኩህን ሁሉ እስካደርግልህ ድረስ አልተውህም” አለው፡፡ ያዕቆብም ከእንቅልፍ ተነሥቶ በእውነት እግዚአብሔር በዚህ ስፍራ አለ፤ እኔ አላወቅሁም ነበር፡፡ ይህ ሥፍራ እንዴት ያስፈራል? ይህ ስፍራ የእግዚአብሔር ቤት ነው እንጂ ሌላ አይደለም፤ ይህችም የሰማይ ደጅ ናት፡፡ ያዕቆብም ማልዶ ተነሣ ተንተርሷት የነበረችውንም ድንጋይ ወስዶ ሐውልት አድርጎ አቆማት፤ በላይዋም ዘይት አፈሰሰባት፡፡ ያዕቆብም ያን ሥፍራ ቤቴል ብሎ ጠራው አስቀድሞ ግን የዚያ ከተማ ስም ሎዛ ነበር፡፡ ያዕቆብም ስዕለትን ተሳለ፡፡ እግዚአብሔር ከእኔ ጋር ቢሆን በምሄድበት መንገድ ቢጠብቀኝ፣ የምበላውን እንጀራ የምለብሰውን ልብስ ቢሰጠኝ ወደ አባቴ አገር በሰላም ቢመልሰኝ እግዚአብሔር አምላኬ ይሆንልኛል፡፡ ለሐውልት ያቆምኳት ይህች ድንጋይ የእግዚአብሔር ቤት ትሆንልኛለች፤ ከሰጠኸኝ ሁሉ ለአንተ ከአስር እጅ አንዱን እሰጥሃለሁ አለ፡፡ እግዚአብሔርም ስእለቱን ሰምቶ ሁሉንም ፈጸመለት ወደ አጎቱ ወደ ላባ ደርሶ ሚስት አግብቶ ብዙ ልጆችን ወልዶ እንዲሁም ብዙ ባሮችን እና ሀብት ንብረት አፍርቶ ወደ አባቱ ሀገር ሲመለስ እግዚአብሔር አምላክ ተገለጠለትና “ወደ ቤቴል ውጣ በዚያም ኑር” ብሎ አዘዘው ዘፍ.28፥10-20፣ ዘፍ.35፥1፡፡
ለመሆኑ ይህች ቤቴል ማን ናት? እግዚአብሔር አምላክ ለጊዜው ያዕቆብና ቤተሰቡ እንዲኖሩባት ለፍጻሜው ሁላችንም እንድንኖርባት የታዘዝንባት ቤቴል ምስጢራዊ ትርጉሟ ምን ይመስላል? አባቶቻችን እንዲህ ይተረጉሙታል፡፡

Friday 22 February 2013

ጾመ ነነዌ

ጾመ ነነዌ




እግዚአብሔር ነብዩ ዮናስን ወደ ነነዌ ምድር በኃጢአታቸው ምክንያት ሊያመጣው ካሰበው የእሳት ዝናም እንዲትርፉ ቢልከው እግዚአብሔርን ቸርነት ስለሚያውቀው ቸርነትህ ከልክላህ ሳታጠፋቸው ብትቀር እኔ የሐሰት ነቢይ እባል የለምን? ብሎ ሰግቶ ወደ ተርሴስ ሃገር ከነጋዴዎች ጋር ተሳፈረ።
እግዚአብሔርም ታላቅ ማዕበልን አስነሳ በመርከቧ ያሉ ሰዎችም እርስ በራሳቸው ዕጣን ተጣጥለው በዮናስ ላይ ወደቀ። እርሱም ያደረገውን ሰለሚያውቅ ሌሎቹ በውሰጥ ያሉት እንዳይጣል ብዙ ጥረት ቢያደርጉም የግድ መጣል ስለ ነበረበት ወደ ባሕር ተጣለ። እግዚአብሔርም ታላቅ ዓሣ አንበሪን አዘጋጅቶ በከርሠ ዓሣ አንበሪ ሦስት መዓልት ሦስት ሌሊት ቆይቶ በሦስተኛው ቀን በአንጻረ ነነዌ ተፍቶታል። በግድም ቢሆን ስለ ሚመጣባቸው መዓት አስተምሯል። ትንቢተ ዮናስ ምዕራፍ 1 እና 2 ነብዩ ዮናስ ለመጀመርያ ጊዜ ወደ አሕዛብ ሀገር የተላከ ነቢይ ነው።

ዮናስ ማለት ርግብ ማለት ነው። ርግብ የዋህ እንደሆነች እሱም የዋህ ነውና ይህ ቅጽል ተቀጽሎለታል። የርግብ የዋህነት እንደምን ነው ቢሉ በማየ አይኅ (በጥፋት ውሃ )ጊዜ በእባብ አፍ ውስጥ እንቁላል ጥላለች።

Tuesday 12 February 2013

እንጦንዮስ አበ መነኰሳት

እንጦንዮስ አበ መነኰሳት አትም ኢሜይል

ጥር 22 ቀን 2005 ዓ.ም.
  • ምንጭ፡- የበረሃው ኮከብ ቅዱስ እንጦንዮስ መጽሐፍ
ጨለማ በዋጠው በግብፅ በረሃ ውስጥ ለብዙዎች አርዓያ በሆነ የእምነት ገድል የቅድስናን ብርሃን በማብራቱ የበረሃው ኮከብ ብለው ብዙዎች ይጠሩታል፡፡

kiduse entonseብፁዐዊ ቅዱስ እንጦንስ በምንኩስና ሕይወት ለመኖር ከጌታችን ከመድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተማረው አብነታዊ ትምህርት (ማቴ.4፥1-10) ከዚህ ዓለም ተድላና ደስታ በመራቅ ከሰዎች ሁሉ ተለይቶ ፍጹም መንፈሳዊ ተጋድሎን በመጋደል በተወለደ በ106 ዓመቱ ጥር 22 ቀን በ356 ዓ.ም. ከዚች ዓለም በሥጋ ተለይቷል፡፡ “ክቡር ሞቱ ለፃድቅ በቅድመ እግዚአብሔር” “የፃድቅ ሰው ሞቱ በእግዚአብሔር ፊት የከበረ ነው” በማለት ክቡር ዳዊት እንደተናገረው፣ “ቅድስት ቤተ ክርስቲያን የቅዱሳን የልደታቸውን ጊዜ፣ የተጋድሏቸውን ሁናቴ፣ ቃል ኪዳን የተቀበሉባቸውንና ያረፉባቸውን ዕለታት በክብር ታስባለች፡፡ ይህም በቅዱስ መጽሐፋችን “የፃድቅ መታሰቢያ ለበረከት ነው”(ምሳ.10÷7)፡፡ በመሆኑም “ስለ ፅድቅ የሚሰደዱ ብጹአን ናቸው ÷ መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ ናትና” (ማቴ.5÷8) በሚለው በጌታችን ትምህርት የዚችን ዓለም ጣዕም ንቆ በምናኔ በመኖር ለመነኮሳት አብነት የሚሆናቸውን የቅዱስ እንጦንስን ዜና ሕይወት አቅርበናል፡፡ለመሆኑ ቅዱስ እንጦንስ ማን ነው? አስተዳደጉና የፈጸማቸው አገልግሎቶቹ ምን ይመስላሉ?

ልጅነት
እንጦንዮስ/እንጦንስ/ ትውልዱ ግብጻዊ ሲሆን ቤተሰቦቹም መልካሞችና ባለጸጎች ነበሩ፡፡ እነርሱም በሕፃንነት ኑሮው ከቤቱና ከወላጆቹ በስተቀር ምንም አላወቀም፡፡ እያደገና ዕድሜው እየጨመረ ሲሄድ ትምህርት ቤት አልገባም ነበር፡፡ ይህም ከሌሎች ልጆች ጋር ጓደኝነት ባለመፈለጉ ነበር፡፡

Thursday 31 January 2013

ዕረፍታ ለእግዝእትነ ቅድስት ድንግል ማርያም (ጥር 21)


ማርያም ማለት መርሕ ለመንግሥተ ሰማያት ማለት ነው፡፡ ምዕመናንን እየመራች ወደ መንግስተ ሰማያት ታስገባለችና፡፡ አንድም ፍጽምት ማለት ነው፡፡ በሥጋም በልቦናም ንጽሕት ናትና፡፡ ማርያም ማለት ልዕልት ማለት ነው፡፡ ከፍጡራን በላይ ናትና፡፡ ‹‹ማር›› በምድር ‹‹ያም›› በሰማይ ናት፡፡ ማር በምድር ተወዳዳሪ የሌለው ምግብ ነው፡፡ ያም በሰማይ ቅዱሳን የሚመገቡት በብሔረ ሕያዋን በብሔረ ብፁዓን ያሉ ቅዱሳን የሚመገቡት ጣፋጭ ምግብ ነው፡፡ የእመቤታችን ርህራሄዋ በምድርም በሰማይም ሁሉ ጣፋጭ ነውና ማርያም ተባለች፡፡እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በዚህ ምድር ላይ 64 ዓመት ኖራ ጥር 21 እሑድ ቀን ጌታ እልፍ አእላፍ መላእክቱን አስከትሎ መጥቶ እናቴ ሆይ ከዚህ ዓለም ድካም ላሳርፍሽ መጣሁ ቢላት ልጄ ሰማይና ምድር የማይወስኑህን ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በማኅፀኔ ተሸክሜ፣ በድንግልና ወልጄህ እሞታለሁን? አለችው፡፡ በሲኦል የሚሰቃዩ ነፍሳትን አሳይቶ እናቴ ሆይ ሞትሽ ለእኚህ ቤዛ ይሆናቸዋል አላት፡፡ እመቤታችንም እኚህን ከማርክልኝስ ይሁን አለችው፡፡ ቅድስት ሥጋዋንም ለይቶ በቃለ አቅርንት በዝማሬ መላእክት አሳረጓት፡፡

Wednesday 23 January 2013

አቡነ ሐራ ድንግል

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን::

ከሁሉ አስቀድመን የአንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያንልጆች የሆን እኛ የክርስቶስ ወገኖች ሰዎች ነ...ገርን ከማብዛት በማሳነስ ነገርን ከማስረዘም በማሳጠር ክቡርና ልኡል ትሩፋቱ ፍፁም ገድሉም ብዙ የሆነ ምስራቃዊ የክብር ኮከብ አርያማዊ የፅድቅ ጸሀይ የኦርቶዶክሳዊ ሀይማኖት ዓምድ የመንፈሳዊ ምግባርማደሪያ የሆነየአባታችን ሐራ ድንግልን ገድሉንና ትሩፋቱን የፅድቁንም ስራ እንጽፍ ዘንድ ህይወትን ሰጪ በሚሆን በባታዊ አድሮ በሚኖር ገዳማዊውን በሚጎበኝ የአለማዊውንም ሰው በደል በመለኮታዊ ስልጣኑ በሚያስተሰርይ በአምላክ ፈቃድ ለመጀመር ተግተን ተመኘን::

ለሁላችንም የጥምቀት ልጆች ከኦሪታዊው ከሙሴና ከወንጌላዊው ከዮሀንስ ጋር አሸናፊ እግዚአብሄርን በቀናች ሀይማኖትና በመልካም ምግባር ካገለገሉት ከጻድቃንና ከመነኮሳትም ጋር ሰማያዊ የነፍስ ደስታ እድልን ያድለን ክብር ምስጋና ለእርሱ ይሁን ለዘላለሙ አሜን::

አቡነ ሐራ ድንግል

አስቀድመን በመጻፋችን የጠራነው የዚህ ጻድቅ አባቱና እናቱ በላጉና ምድር ይኖሩ ነበር :: እርስዋም ከደራ ምድር አንድ ክፍል ናት::

Friday 18 January 2013

እውነት እውነት እልሀለሁ ሰው ከውሃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም።” ዮሐ ፫፡፭

“እውነት እውነት እልሀለሁ ሰው ከውሃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም።” ዮሐ ፫፡፭ አትም ኢሜይል

በይበልጣል ጋሹ
ጥር ፲ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም.
timiket 2005ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመዋዕለ ስጋዌው በምድር በነበረበት ዘመን ከፈጸማቸው እና ለሰው ልጅ ከሰጣቸው ሚስጢራት አንዱ ጥምቀት ነው። “ጥምቀት” የሚለው ቃል አጥመቀ ከሚለው የግዕዝ ግሥ የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም፣ መነከር፣ መዘፈቅ፣ መደፈቅ፣ መላ አካልን በውሃ ውስጥ ማስገባት ማለት ነዉ። በሚስጢራዊ ትርጉም ደግሞ ብዙ ምሳሌዎች አሉት። ከምሳሌዎች መካከልም፦ የአብርሃም ከሃገሩ መውጣትና ዮርዳኖስን ተሻግሮ ወደ ከነዓን መግባት የጥምቀት ምሳሌ ነው። ምዕመናን ከዓለመ ኃጢአት ወጥተው የመንግሥተ ሰማያት ዜጎች የሚሆኑት በጥምቀት ነውና። ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ በ፩ጴጥ ፫፡፳፩ ላይ ኖህ ከጥፋት ውሃ የዳነባትን መርከብ የጥምቀት ምሳሌ ናት ብሏታል ምክንያቱም ምዕመናን ከጥፋት የሚድኑት በጥምቀት ስለሆነ። እንዲሁም ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ በ፩ቆሮ ፲፡፩ እስራኤል ከግብፅ የባርነት ቀንበር ተላቀው የኤርትራን ባሕር ተሻግረው ወደ ምድረ ርስታቸው ያደረጉትን ጉዞ የጥምቀት ምሳሌ አድርጎ ተናግሯል፤ምእመናን ባሕረ ኃጢአትን ተሻግረው ምድረ ርስት መንግሥተ ሰማያት የሚወርሱት በጥምቀት ነውና። ጥምቀት ከእግዚአብሔር ዳግም የምንወለድበት፣የቤተ ክርስቲያን አባል የምንሆንበት፣ የኃጢያት ስርየት የስጋ ፈውስ የምናገኝበት ረቂቅ ምስጢር ነው።
1. የጥምቀት መስራቹ ማነው?
አግዚአብሔር ቀድሞ በነቢያት ያናገረውን ለመፈፀም ከቅድስት ድንግል ማርያም በኅቱም ድንግልና ተጸንሶ በኅቱም ድንግልና ተወለደ።ሉቃ ፪፡፩ ከኃጢአት በስተቀር እንደኛ ሰው ሆኖ ሕገ ጠባዕያዊን እና ሕገ መጽሐፋዊን እየፈጸመ ቀስ በቀስ አደገ። እንደዚህ እያለ ሠላሳ/30/ ዘመን ሲሞላው በዘመነ ሉቃስ በዕለተ ማክሰኞ ሌሊት 10 ሰዓት ጥር 11 ቀን በዮሐንስ እጅ ይጠመቅ ዘንድ ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ ሄደ። ወደ ዮርዳኖስ ወንዝም ሄዶ ዮሐንስን አጥምቀኝ አለው። ዮሐንስም መልሶ እኔ ሎሌህ በአንተ በጌታዬ እጠመቅ ዘንድ ይገባኛል እንጂ አንተ በእኔ ትጠመቃለህን? አለው። ጌታችንም ሕግን ልንፈጽም ይገባናልና አጥምቀኝ አለው። ዮሐንስም በአብ ስም እንዳላጠምቅህ አብ በአንተ ህልውና ነው፣ በወልድ ስም እንዳላጠምቅህ ወልድ አንተ ነህ በማን ስም አጠምቅሀለው አለው? “ወልዱ ለአብ ከሣቴ ብርሀን ተሣሃለነ” ብርሃንን የምትገልጽ የአብ የባህርይ ልጅ ይቅር በለን እያልክ አጥምቀኝ አለው። ዮሐንስም ክርክሩን አቁሞ አጠመቀው። ማቴ ፫፡፲፫-፲፯ በዚህ መሠረት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በ30 ዘመኑ በዮሐንስ እጅ በዮርዳኖስ ወንዝ ተጠመቀ። የሠው ልጅ ሁሉ ይድን ዘንድ እና ዳግመኛ ከሥላሴ ይወለድ ዘንድ እርሱ ተጠምቆ ጥምቀትን ሰጠን። በመሆኑም የጥምቀትን ምስጢርና አስፈላጊነት ያስተማረ፤ ጥምቀትንም የመሰረተው እርሱ እራሱ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ከዚያም “ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አጥምቁ” በማለት ለሐዋርያት ሥልጣንና ትዕዛዝ ሰጥቷል። ማቴ ፳፰፡፲፱
2. አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለምን ተጠመቀ፤
እግዚአብሔር አምላክ የሰውን ልጅ መጥፋት ተመልክቶ አዳምን ያድነው ዘንድ ወደደ እንደኛ ሰው ሆኖ ተወለደና አደገ። አዳምን ሲፈጥረው የ30 ዓመት ወጣት አድርጎ ነበርና ያጣኃውን ልጅነት እኔ በ30 ዘመኔ ተጠምቄ በጥምቀት እመልስልሃለሁ ሲለው በ30 ዘመኑ በዮርዳኖስ ወንዝ ተጠመቀ። ቅድስት ቤተ ክርስቲያን የምታስተምራቸዉን የጌታችን ጥምቀት ምክንያቶች እንደሚከተለው እናያለን፦
ሀ) አርዓያ ለመሆን
እርሱ በዮሃንስ እጅ ተጠምቆ እናንተም እንደዚህ ብትጠመቁ ልጅነትን ወይም ከሥላሴ መወለድን ታገኛላችሁ ለማለት ነው። እሱማ እፀድቅ አይል ጻድቅ፣ እከብር አይል ክቡር፣ እነግስ አይል ንጉሥ ነውና ለእኛ አርያ ለመሆን ብሎ ተጠመቀ እንጂ።
ለ) ሚስጢረ ሥላሴን ለማስረዳት
በመጽሐፍ ቅዱስ በተለያየ ቦታ ላይ የተገለጸዉ የእግዚአብሔር አንድነት ሦስትነት በጥምቀት ጊዜም ሰው በሚረዳው መጠን ተገልጧል። ይህም እግዚአብሐር አብ በደመና ሆኖ “በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው” እያለ ለወልድ ሲመሰክር፤ እግዚአብሐር ወልድ በዮርዳኖስ ወንዝ በዮሐንስ እጅ ሲጠመቅ፤ መንፈስቅዱስ በርግብ አምሳል በወልድ ላይ ሲወርድ፤ ሚስጢረ ሥላሴ ወይም የእግዚአብሐር ሦስትነት ማለትም አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ ለሰዉ በሚረዳዉ መልኩ ተገለጠ። ማቴ ፫፡፲፫-፲፯
ሐ) ትንቢቱንና ምሳሌውን ለመፈፀም
እግዚአብሔር አምላክ የተናገረውን እና በነቢያት ያናገረውን አያስቀርምና ቃሉን ለመፈፀም በዮርዳኖስ ተጠመቀ። ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት በመዝሙሩ “አቤቱ ውሆች አዩህ፡ ውሆችም አይተውህ ፈሩ ፡ጥልቆች ተናወጡ ውሆችም ጮሁ” መዝ ፸፮፡፲፮ እንዲሁም ነብዩ ሕዝቅኤል እንደተናገረው “ጥሩ ውሃንም እረጭባችኋለሁ እናንተም ትጠራላችሁ ከርኩሰታችሁም ሁሉ አጠራችኋለሁ አዲስ መንፈስ በውስጣችሁ አኖራለው” ሕዝ ፴፮፡፳፭ ብሎ በነቢያት ያናገረውን ለመፈፀም በዮርዳኖስ ወንዝ ተጠመቀ።
3 ዮርዳኖስ ወንዝንስ ለምን መረጠ
በዮርዳኖስ ወንዝ የተጠመቀበት ምክንያትም እንደሚከተለው እናያለን፦
v ለዮርዳኖስ የተነገረውን ትንቢት ለመፈፀም በዮርዳኖስ መጠመቅ አስፈለገው። ትንቢቱም “አንቺ ባሕር የሸሸሽ፡ አንቺም ዮርዳኖስ ወደ ኋላሽ የተመለሽ ምን ሁናችኋል?” መዝ ፻፲፫፡፭ በማለት ስለ ዮርዳኖስ የተነገረውን ትንቢት ለመፈፀም በዮርዳኖስ ተጠመቀ።
v ምሳሌውን አማናዊ ለማድረግ፤ ዮርዳኖስ ምንጩ አንድ ነው፣ ዝቅ ብሎ ግን በደሴት ይከፈላል፣ ከታች ወርዶ ይገናኛል። ዮርዳኖስ ከላይ ምንጩ አንድ እንደሆነ የሰው ሁሉ ምንጩ አንድ አዳም መሆኑን፣ ዝቅ ብሎ በደሴት መከፈሉ እስራኤል በግዝረት አሕዛብ በቁልፈት የመለየታቸው፣ ከታች ወርዶ መገናኘቱ እና ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመገናኛው ላይ መጠመቁ ሕዝብና አሕዛብን በጥምቀት አንድ ሊያደርግ መምጣቱን ያጠይቃል። እንዲሁም አባታችን ኢዮብ ከደዌው የዳነው በዮርዳኖስ ወንዝ ተጠምቆ ነው። ኢዮብ የአዳም ምሳሌ ነው፤ ደዌው የመርገመ ሥጋ የመርገመ ነፍስ ምሳሌ ነው፤ ዮርዳኖስ የጥምቀት ምሳሌ ነው። የአዳም ዘር ከማኅፀነ ዮርዳኖስ በጥምቀት ዳግም ተወልዶ ከመርገመ ሥጋ ከመርገመ ነፍስ ይላቀቃል ብሎ በዮርዳኖስ ተጠመቀ። ኤልያስ ዮርዳኖስን ተሻግሮ ወደ ብሔረ ሕያዋን አርጓል። ምዕመናንም አምነው ተጠምቀው ገነት መንግስተ ሰማያት የመግባታቸውን ምሳሌ ለማስረዳት አምላካችን በዮርዳኖስ ተጠመቀ።
v የእዳ ደብዳቤያችንን ይደመስስልን ዘንድ፦ ዲያብሎስ የጨለማ መጋረጃ ጋርዶ በአባታችን አዳም እና በእናታችን ሔዋን ስቃይ መከራ አፀናባቸው ስመ ብኩርናችሁን ጽፋችሁ ብትሠጡኝ ፍዳውን አቀልላችኋለሁ አላቸው። እነሱም ስቃዩ እና መከራው የቀለለላቸው መስሏቸው “አዳም ገብሩ ለዲያብሎስ ፤ ሔዋን ዓመቱ ለዲያብሎስ” አዳም የዲያብሎስ ባርያ ሔዋን የዲያቢሎስ ገረድ ብለዉ ጽፈዉ ሰጡት። እሱም በሁለት ገጽ አድርጎ አንዱን በሲኦል አንዱን በዮርዳኖስ አስቀመጠው። ከአምላካችን የሚሰወር ነገር የለምና በዮርዳኖስ የጣለውን ጌታችን በጥምቀቱ ጊዜ እንደሰውነቱ ረግጦ እንደአምላክነቱ አቅልጦ ለማጥፋት ሲል በዮርዳኖስ ተጠመቀ። በሲኦል ያስቀመጠውን ጌታችን በዕለተ ዓርብ በአካለ ነፍስ ወርዶ ነፍሳትን ሲያወጣ በመለኮታዊ ጥበቡ አጥፍቶላቸዋል።
ወነዓምን በአሃቲ ጥምቀት
አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአይሁድ መምህር ለኒቆዲሞስ “እውነት እውነት እልሀለሁ ሰው ከውሃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም።” በማለት ዳግም ልደት ከውሃና ከመንፈስ የሚገኝ መሆኑን እና የጥምቀትን አስፈላጊነት በሚገባ አስረድቶታል። እኛም ዛሬ ይህንን አምላካዊ ቃል መሠረት አድርገን ጌታ በዕለተ ዓርብ ስለኛ በተሰቀለ ጊዜ በፈሰሰው ማየ ገቦ እንጠመቃለን ስንጠመቅም ወንዶች አዳም ተፈጥሮ ገነት በገባበት በ40ኛው ቀን ሴቶች ሔዋን ተፈጥራ ገነት በገባችበት በ80ኛው ቀን ቤተ ክርስቲያን ሥርዓተ ጥምቀትን በመፈጸም የመንፈስ ቅዱስ ልጅነትን ታሰጠናለች/ ኩፋሌ ፬፡፱/። ከዚህም ሌላ ወንድ የወለዱ በአርባ/40/ ሴት የወለዱ በሰማንያ/80/ ቀን ሕፃኑን ወደ ቤተ መቅደስ ማቅረብ እንዳለባቸው ታዝዟል/ዘሌ ፲፪፡፩-፰/ ውንድ የወለዱ ሴቶች ከደመ ሕርስ የሚነጹት ባርባ፤ ሴት የወለዱ ደግም በሰማንያ ቀን ነውና ። ይህ በብሉይ ኪዳን የነበረው ሥርዓት በአርባ ቀን በሰማንያ ቀን ለሚደረገው የክርስቲያን ልጆች ጥምቀት ምሳሌ ነው። ሕፃናቱ ወደ እግዚአብሔር ፊት መቅረብ የሚጀምሩት በዚህ ቀን ነውና ። እዚህ ላይ በእምነት የተለዩን ወገኖቻችን በህጻናትጥምቀት ላይ ጥያቄ ያነሳሉ። ቤተ ክርስቲያናችን ግን መጽሐፍ ቅዱሳዊ መልስ ሰጥታ ትክክለኛነቱን ታረጋግጣለች። “ህፃናት ወደ እኔ ይመጡ ዘንድ ተዋቸው አትከልክሏቸው መንግስተ ሰማያት እንደእነርሱ ላለች ናትና” ማቴ ፲፱፡፲፬ ብሎ አምላካችን በመዋዕለ ስብከቱ ሕፃናቱን ባርኮ በማነኛውም የቤተ ክርስቲያን በረከት ተካፋይ መሆን እንዳለባቸው ለሐዋርያትና ለምእመኑ በሚገባ አስተምሯል። እስኪ አንድ መጻፍቅዱሳዊ እና የጥምቀት ምሳሌ የሆነውን ግዝረትን እናንሳ አብርሃም በእግዚአብሔር ባመነ ጊዜ ሽማግሌ ነበር። ነገር ግን ለማመኑ ምልክት እንዲሆነው ተገዘር ተባለ ተገዘረ። ከዚህ በኋላ የአብርሃም ዘሮች የሆኑ ሁሉ በስምንተኛ ቀናቸው የሚገዘሩት የአብርሃም ልጆች ስለሆኑ ነው። ታድያ እንደ አብርሃም ሳያምኑ ሕፃናት ለምን ተገዘሩ??? በቤተ ክርስቲያንም ሕፃናት የሚጠመቁት ከክርስትያን ቤተሰብ ስለተወለዱ ነው። ጌታችንም በወንጌሉ ሂዱና በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው አሕዛብን ሁሉ አስተምሩ ያዘዝኋችሁንም እንዲጠብቁ አስተምሩአቸው። ባለው መሰረት ቤተ ክርስቲያናችን ለህጻናት ጥምቀትን አስቀድማ ታስተምራለች። ማቴ ፳፰፡፲፱
“ወነአምን በአሐቲ ጥምቀት ለስርየተ ኃጢአት” ኃጢአት በሚሰረይባት በአንዲት ጥምቀት እናምናለን ተብሎ በጸሎተ ሃይማኖት ላይ አባቶቻችን በደነገጉልን መሰረት በጥምቀት ከአብራከ መንፈስ ቅዱስ ዳግም ልደትን እንደምናገኝ እና የኃጢአት ስርየትም እንደሚገኝ ያስረዳናል። “አሁን ለምን ትዘገያለህ ተነሳና ስሙን እየጠራህ ተጠመቅ ከኃጢአትህም ታጠብ” ሐዋ ፳፪፡፲፩ ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ ኃጢአቱ የተወገደለት የእግዚአብሔር አገልጋይ እንዲሆን በተጠራ ጊዜ ሳይሆን በተጠመቀ ጊዜ ነው። ከዚህ ላይ የምንረዳው በጥምቀት ኃጢአታችን እንደሚሰረይልን አምነን ከመከራ ስጋ ከመከራ ነፍስ መዳን የምንችልበት መሆኑና በጥምቀት ኃጢአታችንን አስወግደን ከእግዚአብሔር ጋር ህብረት ይኖረናል ከእርሱም ጋር እንሞታለን ከእርሱም ጋር እንነሳለን።ለዚህም ነው ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ጥምቀትን በሞትና በመቃብር መስሎ ያስተማረን/ሮሜ ፮፡፫/ በሞት ጊዜ ነፍስና ስጋ እንደሚለያዩ በጥምቀትም አሮጌው ሰውነት ይሞታል ይቀበራል አዲሱ ሰውነት አዲስ ሕልውና ህይወት ይጀምራል። ማንኛውም ክርስቲያን በማንኛውም ነገር ክርስቶስን ሊመስል ይገባዋል። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “እኔን ምስሉ” ብሏልና ሞቱን በሚመስል ሞት ከእርሱ ጋር ከተባበርን ትንሳኤውን በሚመስል ትንሳኤ ደግሞ ከእርሱ ጋር እንተባበራለን። ከክርስቶስ ጋር የምንሞተውና የምንቀበረው ደግሞ በጥምቀት ነው።
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለሰው ልጅ ድኅነት ከዮሐንስ እጅ ይጠመቅ ዘንድ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ ያደረገውን አምላካዊ ጉዞ ለማሰብ በየአመቱ ጥር 10 ቀን ታቦታቱ በካህናትና በምእመናን ታጅበው ወደ ባህረ ጥምቀት በመጓዝ አምሳለ ዮርዳኖስ በሆነውና በተዘጋጀላቸው ቦታ በክብር ያርፋሉ። ሌሊቱን በሙሉ በማኅሌትና በቅዳሴ በዓሉ እየተከበረ ያድራል። ጧት ጥር 11 ቀን የበረከት ጥምቀት ከተፈፀመ በኋላ በደማቅና በልዩ ሥነ ሥርዓት በስብሐተ እግዚአብሔር በዓሉ ይከበራል። ታቦታቱም በማህሌት፣ በመዝሙርና በእልልታ ታጅበው ወደ መንበራቸው በክብር ይመለሳሉ። ይህ ዕለት ከባርነት ነጻ የወጣንበት፣ የእዳ ደብዳቤያችን የተደመሰሰበት፣ ከእግዚአብሔር ጋር አንድ የሆንበት ስለሆነ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን የጥምቀትን ሥርዓትና ምስጢር ለዘመናት ስትፈፅም ዛሬም እየፈፀመች ወደፊትም በመፈፀም ትኖራለች። ምክንያቱም ከላይ በትምህርታችን እንዳየነው ለሰው ልጅ የድኅነት በሩ ዳግም በጥምቀት ከአብራከ መንፈስ ቅዱስ መወለድ ነው ከዚህ ውጪ የእግዚአብሔርን መንግሥት መውረስ አይቻልምና።
እኛም የአዳም ልጆች ይህን የቤተ ክርስቲያን ሥርዓትና ህግ የማስጠበቅ ግዴታና ኃላፊነት እንዳለብን ተገንዝበን በ40 እና በ80 ቀን ያገኘነውን የእግዚአብሔር ልጅነት አዳምን ያሳተ ዲያብሎስ ልጅነታችንን እንዳይነጥቅብን አጥብቀን መያዝ ይገባናል። ሌሎች ወገኖቻችንም የዚህ ታላቅ ጸጋ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ እንድንችል የእግዚአብሔር መልካም ፈቃድ ይሆንልን። ለዚህም በጾምና በጸሎት እንድንተጋ አምላከ ቅዱሳን ልዑል እግዚአብሔር ይርዳን። በዓሉን የሰላም፣የፍቅር፣ የአንድነት፣ የመተሳሰብና የበረከት ያድርግልን። አሜን። ወስብሐት ለእግዚአብሔር።+++
1. የጥምቀት መስራቹ ማነው?
አግዚአብሔር ቀድሞ በነቢያት ያናገረውን ለመፈፀም ከቅድስት ድንግል ማርያም በኅቱም ድንግልና ተጸንሶ በኅቱም ድንግልና ተወለደ።ሉቃ ፪፡፩ ከኃጢአት በስተቀር እንደኛ ሰው ሆኖ ሕገ ጠባዕያዊን እና ሕገ መጽሐፋዊን እየፈጸመ ቀስ በቀስ አደገ።

Thursday 10 January 2013

ቅድስት ወለተ ጴጥሮስ አትም ኢሜይል

አባቷ ባሕር አሰግድ እናቷ ደግሞ ክርስቶስ አዕበያ ይባላሉ። ትውልዷ ከዳሮ /ምስራቅ ኢትዮጵያ/ ወገን ነው። ወንድሞቿ ዮሐንስና ዘድንግል በንጉሥ ሱስንዮስ ጊዜ ታላላቅ ባለስልጣናት ነበሩ። እናት አባቷ በህግ በስርዓት ካሳደጓት በኋላ ሥዕለ ክርስቶስ የሚባል የስስኑዮስ የጦር አበጋዝ ቢትወደድ አግብታ 3 ልጆች መውለድዋን ገድሏ ይናገራል። ይህ ቢትወደድ ይኖርበት የነበረው ግንብ ቤት ፍራሽ እስከ አሁን ድረስ በጋይንት ስማዳ ይታያል።
ወለተ ጴጥሮስ ከቢትወደድ ሥዕለ ክርስቶስ ጋር በሰላም በመኖር ላይ እያለች ንጉሡ አጼ ሱስንዮስ የተዋሕዶ ሃይማኖቱን ቀይሮ በሮማውያን ሀሰተኛ መምህራን በመታለል ካቶሊክነትን ተቀብሎ የኢትዮጵያ ህዝብም ካቶሊክ እንዲሆን ዐወጀ። በዚህ ዐዋጅ የተነሣ በንጉሡ ደጋፊዎችና የቀደመ ሃይማኖታችንን አንለቅም ባሉት እውነተኛ የተዋህዶ ምዕመናን መካከል ታላቅ ጠብ ሆነ።